ጎጃምን ምታ ጎንደርን ምታ
ጎጃምን ምታ ጎንደርን ምታ
አንድ በጣም ወፍራም ሴትዮ የእንጦጦን ጋራ በእግራቸው ለመውጣት ይያያዙታል ። ሲደክማቸው ኋላቸውን ዞር በማለት እየተመለከቱ በማረፍ ሲጓዙ አንዴ ፈሳቸውን ብው ሲያደርጉ «ጎጃምን ምታ !» ይላሉ ። አሁንም ወጥተው ወጥተው ሲደክማቸው ዞር ብለው በማየት ፈሳቸውን « ብም ..ብም ..ቡዋ !» ሲያደርጉት «ጎንደርን ምታ !» ይላሉ። በመጨረሻም ዞር ዞር ብለው በመመልከት ፈሳቸውን «ጣጣጣጣጣ ..ጥጥጥጡዋ » ሲያደርጉት «ትግራይ ምታ !» ብለው ዞር ሲሉ አንድ ዱርዬ ተማሪ ከኋላቸው ቆሞ ያዩታል ። ከዚያም «ውይ ! ልጄ የት ነበርክ ?» ሲሉት «ጎጃምም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ : ጎንደርም ትግራይም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ» ሲላቸው : «ውይ ልጄ ! እናትም የለህ ?» ሲሉት ምን እንዳለ ታውቂያለሽ ? ቂቂቂቂቂ ... «ታዲያ እናት ቢኖረኝ ይታራብኛል እንዴ ?» ብሏቸው አረፈው እልሻለሁ።