ግራዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ግራዋ በኢትዮጵያ ውስጥ ባህላዊ መጠጦችን ከማዘጋጀታቸው በፊት ለዕቃ ማጠቢያነት ያገለግላል። ለምሳሌ ጠላ፣ጠጅ ከማዘጋጀታቸው በፊት እቃወቹ በግራዋ ቅጠል ይታጠባሉ። ከዚህች በተጨማሪ ሰዎች ለቁርባ በሽታ፣ ለሆድ ቁርጠት እንደ መድሃኒት ይጠቀሙበታል ።

ግራዋ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ለማስተካከል

ቊጥቋጥ ወይም ትንሽ ዛፍ፣ እስከ 10 m ድረስ ሊቆም ይችላል።

ሲያብብ ንቦቹ ይወዱታል።

አስተዳደግ ለማስተካከል

ቶሎ በቀላል በራሱ ይታደጋል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር ለማስተካከል

በተለይ በጠፍ መሬት፣ በደን ዳርቻ፣ በውድማ በ1700-3000 ሜትር ከፍታ ያድጋል።

የተክሉ ጥቅም ለማስተካከል

የውስጡ ፈሳሽ ለሚያስቀምጥ መድሃኒት ይጠቀማል። ደረቁ አበባ የሆድ ቁርጠት ለማከም ተጠቅሟል። ወባን ደግሞ ለማከም እንደ ተጠቀመ ይነገራል።

ቅጠሎቹ አንዳንዴ በጌሾ ፈንታ ጠላን ለመሥራት ይጠቀማሉ። የተበሰሉ ቅጠሎቹ ሊበሉ ይቻላል።[1]

ቅጠሉም ተድቅቆ በውሃ ለኮሶ ትል፣ ለወስፋት፣ እና ለሆድ ቁርጠት ይጠጣል።[2]

የቅጠሉም ጭማቂ ለአንጓ ብግነት («እንጥል ሲወርድ») እንደ ተጠጣ ተዘግቧል።[3]

እንዲሁም የግራዋ፣ የሰንሰልና የእምቧጮ ቅጠል ጭማቂ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለወባ ይሰጣል።[4]

  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
  4. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች