አቶ ጌትነት ተስፋማርያም በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የሚታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጠኛ ናቸው። አዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱት አቶ ጌትነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዜና እና አምዶች ላይ እየጻፉ ይገኛል። በተለይም ''በየመድሃኒት ቤቱ በግላጭ የሚቸበቸበው ዶናዶል መድሃኒት'' ላይ እና በአፄ ቴዎድሮስ 150ኛ ዓመት የልደት በዓል አስመልክቶ እንዲሁም ''የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተስፋ ይኖረው ይሆን?'' በሚል ርዕስ የጻፏቸውን ስራዎች መጥቀስ ይቻላል። እንዲሁም ''የመቅደላው ምርኮ ልዑል አለማየሁ'' እና ''ህዝቡን ማማረር እስከመቼ'' የተሰኙ እና በርካታ ዜናዎች እና የአምድ ጽሁፎችን ሰርተዋል። በጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወትን የተመለከቱ ጽሁፎች በተለያዩ ጊዜያት ሲያዘጋጁ ይስተዋላል። ለአብነት ''ዘላቂ ድጋፍ የሚሹ ነፍሶች'' በሚል ርዕስ ያቀረቡት ስራ አለ። በአዲስ አበባ የሚኖሩት አቶ ጌትነት በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ናቸው።