ጉድ ታይምዝ (የሺክ ዘፈን)
«ጉድ ታይምዝ» (Good Times) ከ1979 እ.ኤ.አ. (1971 ዓም) የሆነ የሺክ ነጠላ ዘፈን ነው። ከሦስተኛ አልበማቸው ሪስኬ ነው፤ በብዙ አገራት በዚያው አመት እስከ #1 ሥፍራ ድረስ ፈለቀ። ዘፈኑ #1 በሆነበት ወቅት፣ ከጥር 1966 ዓም ጀምሮ የተሠራጨው እጅግ ታዋቂ ቴሌቪዝን ትርዒት «ጉድ ታይምዝ» እንዳጋጣሚ ጨረሰ።
«ጉድ ታይምዝ» | |
---|---|
የሺክ ዘፈን ከሪስኬ አልበም | |
የተለቀቀው | 30 June፣ 1979 እ.ኤ.አ. |
የተቀዳው | 1979 እ.ኤ.አ. |
ስልት | ዲስኮ ሙዚቃ |
ርዝመት | 8:08 (አልበም) 3:24 (7") |
ቋንቋ | እንግሊዝኛ |
አሳታሚ | በርናርድ ኤድዋርድዝ፣ ናይል ሮጀርዝ |
ግጥም | በርናርድ ኤድዋርድዝ፣ ናይል ሮጀርዝ |
ቅንብር | አትላንቲክ ሬኮርድስ |
ዘፈኑ ዓለም ዙሪያ ተወደደና በሂፕ-ሆፕ ሙዚቃ ከዘፈኖች ሁሉ የተቀመሰው ዜማ ሆኗል።
ከዚህም ከጥቂት አመታት በሗላ ደግሞ ከቅድመኞቹ ራፕ ሙዚቃ ዘፈኖች አንዱ የሹገር ሂል ጋንግ ዘፈን «ራፐርዝ ዲላይት» የተባለው ውድ ዘፈን ከዚሁ ዜማ ከተለቀቁት ዋናው ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |