ገቢር ማዳመጥ
ገቢር ማዳመጥ በመመከር፣ በዕርቅና፣ በማሠልጠን ሊጠቀም የሚችል ዘዴ ነው። ገቢር ማዳመጥ ከተገብሮ ማዳመጥ ወይም ዝም ብሎ ከማዳመጥ ይለያል፤ በገቢር ማዳመጥ አዳማጩ ምን ያህል መልእክት የሰማው እንደ መሰለው በድጋሚ ይመልሳል።
«ገቢር ማዳመጥ» ወይም በእንግሊዝኛ «active listening» የሚለው ዘዴ በአሜሪካዊው መምህር ቶማስ ጎርዶን በ1954 ዓም በፈጠረው «የወላጆች ተደማጭነት ማሠልጠን» (Parent Effectiveness Training) ውስጥ ተጀመረ። በ1962 ዓም ባሳተመው መጽሐፍ «የወላጆች ተደማጭነት ማሠልጠን» የገቢር ማዳመጥን ዘዴ አብራራ። ከዚያ በኋላ ዶ/ር ጎርዶን በሌሎች መርሃግብሮችና መጻሕፍት ውስጥ እንደ «የአስተማሮች ተደማጭነት ማሠልጠን»፣ «የመሪዎች ተደማጭነት ማሠልጠን» ዘዴውን አጠቀለለው።
የተናጋሪው አጠቃላይ መልእክት በትክክል ምን እንደ ሆነ አውቆ፣ ገቢር አዳማጩ በመልሱ በራሱ ቃላት ያሳያል። ሆኖም ተናጋሪው ካላሠበው ነገር እንዲራቅ መጠንቀቅ አለበት፣ አለዚያ በአመክንዮ ሀሠት የሰውን ቃል ወደ ሌላ ማዛበቱ ሰውን ፈርቶ አዲስ የገለባ ሰው ሠርቶ እንደ ማጥፋቱ ይሆን ነበር። እንደዚህ እንዳይሆን አንዳንዴ ተንጸባራቂ ማዳመት ወይም ምንም ሳይቀየር መልእክቱን በቀጥታ ማዳገም ይሻላል።
በ1962 ዓም መጽሐፉ፣ ድ/ር ጎርዶን ሲያብራራው የወላጅ ለልጁ ገቢር ማዳመጥ በምሳሌዎች አቀረበ። በመጀመርያው ምሳሌ ወላጁ ገቢር ማዳመጥን አይጠቅምም፦
- ልጅ (12 ዓመት)፦ ወደ ትምህርት ቤት ልሄድ ነው!
- አባት፦ እየዘነበ ነው፣ የዝናብ ልብስሽንም አለበሽም።
- ልጅ፦ አያስፈልገኝም።
- አባት፦ አያስፈልግሽም? እርጥብ ትሆኛለሽ፣ ልብስሽም ይበላሻል፣ ጉንፋንም ታገኛለሽ!
- ልጅ፦ በጣም አይዘንብም።
- አባት፦ አዎ በጣም ይዘንባል!
- ልጅ፦ እኔ ግን የዝናብ ልብስ መልበስ አልፈልግም። ዝናብ ልብስ መልበሱን ጠላሁት!
- አባት፦ አሁኑኑ ተመልሰሽ በቀጥታ የዝናብ ልብስሽን ይዘሽ አድርጊው! በዚህ ዝናብ ውስጥ ያለ ዝናብ ልብስ ወደ ትምህርት ቤት ልትሄጅ አልፈቅድም!
- ልጅ፦ እኔ ግን አልወደውም!
- አባት፦ ግን አትበዪኝ! ካለበሸው እናትሽና እኔ ቅጣት እንሰጣለን!
- ልጅ፦ በቃ አሸነፍክ! ደደቡን ዝናብ ልብስ እለብሰዋለሁ!
በሌላ ምሳሌ ያለ ገቢር ማዳመጥ ልጂቱ ታሸንፋለች፦
- ልጅ፦ ...እኔ ግን የዝናብ ልብስ መልበስ አልፈልግም። ዝናብ ልብስ መልበሱን ጠላሁት!
- አባት፦ እንድትለብሺው እወዳለሁ እንጂ።
- ልጅ፦ ያንን ዝናብ ልብስ እጠላዋለሁ! አለብሰውም! ብታስገዱኝስ እናድዳለሁ!
- አባት፦ በቃ እንግዲህ! ያለ ዝናብ ልብስሽ ወደ ትምህርት ቤት ሂጅ፣ ከዚህ በላይ ክርክር አልፈልግም፣ አንቺ ታሸንፊያለሽ።
በመጨረሻ በ«ገቢር ማዳመጥ» ዘዴ በፍጹም ሌላ መፍትሄ ይደርሳል፦
- ልጅ፦ ወደ ትምህርት ቤት ልሄድ ነው!
- አባት፦ እየዘነበ ነው፣ የዝናብ ልብስሽንም አለበሽም።
- ልጅ፦ አያስፈልገኝም።
- አባት፦ አሁን በሃይል ሲዘነብ ነው መሰለኝ። ልብስሽ ቢበላሽ ወይም ጉንፋን ብታገኚ ለኛም መጥፎ ውጤት ይሆናል።
- ልጅ፦ እኔ ግን የዝናብ ልብሴን መልበስ አልፈልግም።
- አባት፦ ያንን ዝናብ ልብስ መልበስ በእርግጥ አትወጂም ይመስለኛል።
- ልጅ፦ አዎ ልክ ነው፣ ጠላሁት!
- አባት፦ የዝናብ ልብስሽን በውነት ጠላሸው።
- ልጅ፦ አዎ፣ ዝንጉርጉር ነውና!
- አባት፦ ስለ ዝንጉርጉርነት የጠላሽው ነገር አለ?
- ልጅ፦ አዎ፣ በትምህርት ቤት ማንም ሰው ዝንጉርጉርን ዝናብ ልብስ አይለብስም!
- አባት፦ አንቺ ተለይተሽ ብቻ ሌላ ነገር መልበስ አትወጂም...
- ልጅ፦ እኮ አልፈልግም! ሰው ሁሉ ነጭ ወይም ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ ዝናብ ልብስ ይለብሳል።
- አባት፦ ገባኝ። እኛ ግን ችግር በዚህ አለን። አንቺ ዝናብ ልብስሽን ዝንጉርጉር ስለ ሆነ መልበስ አትፈልጊም፤ እኔ ግን ለልብስ ማጽዳት ሂሳብ መክፈል እኮ አልወድም፣ እንዲሁም አንቺ ጉንፋን ብታገኚ አይመችልኝም። ለኛ ሁለታችን ተስማሚ መፍትሄ ማሠብ ትችያለሽ?
- ልጅ፦ ምናልባት ዛሬ የእናቴን መኪና ካፖርት መበደር እችላለሁ።
- አባት፦ እሱ ምን ይመስላል? ዝንጉርጉር አይደለም?
- ልጅ፦ አዎ። ነጭ ነው።
- አባት፦ ዛሬ እንድትለብሺው ትፈቅዳለች መሰለሽ?
- ልጅ፦ እጠይቃታለሁ። (ከአንድ ደቂቃ በኋላ ካፖርቱን ለብሳ ተመለሰች) እናቴ እሺ ትላለች!
- አባት፦ ያው ነገር ላንቺ ደህና ነው?
- ልጅ፦ እኮ፣ ደህና ነው።
- አባት፦ እኔም ድርቅ ሆነሽ እንዲጠብቅሽ አምናለሁ። ስለዚህ ያው መፍትሄ ለአንቺ ደህና ከሆነ ለኔም ደህና ነው።
- ልጅ፦ እሺ ደህና ዋል።
- አባት፦ ደህና ዋይ፣ በትምህርት ቤት መልካም ቀን ይሁንሽ።
- ^ Dr. Thomas Gordon, 1970, Parent Effectiveness Training pp. 153-155, 196-197 (እንግሊዝኛ)