ገላን ተሰማ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው።

የህይወት ታሪክ ለማስተካከል

ገላን ተሰማ ተወልዶ ያደገው በወለጋ ኖኖ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የመጣው በአስር ዓመቱ ነው። በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. በክብር ዘበኛ ጋራዥ ክፍል ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቶ ከሶስት ዓመታት በኋላ ወደ ቲያትር ክፍሉ ተዛውሮ በመሰልጠን ዳንኪረኛ ለመሆን ችሏል።[1]

ገላን እስከ ዛሬ ድረስ የተለያዩ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከእነርሱም መካከል «እንደ ተመኘኋት» የተባለችውን ዜማ በይበልጥ ይወዳታል፤ ገላን በወቅቱ የክብር ዘበኛ አርቲስቶች የዳንኪራ መምህር ነበር። ገላን በዳንኪርተኛነቱ እጅግ የተደነቀና የተፈጥሮ ስጦታ ያለው ነው።[1]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 24". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-17 የተወሰደ.