ጆዋን ሮውሊንግ
ጆዋኔ ጆ ሮውሊንግ (በእንግሊዝኛ: Joanne "Jo" Rowling) (31፣ ጁላይ 1965 እ.አ.አ. ተወለደች) የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነች ታዋቂ ደራሲ ናት። ይች ደራሲ በይበልጥ ሮውሊንግ (J. K. Rowling) በሚለው መጠሪያዋ የምትታወቅ ሲሆን በሃሪ ፖተር መፅሐፍ ተከታታይ ድርሰቶቿ ታላቅ ዝናን አትርፋለች። እነዚህ መፅሐፎቿ የተለያዩ ሽልማቶችን አስገኝተውላታል፤ ከ400 ሚሊዮን በላይ ቅጅዎች ተሽጠዋል በተጨማሪም በመፅሐፎቹ ላይ የተመሠረቱ ሰባት ተከታታይ ፊልሞች ተሰርተዋል። በእነዚህ ፊልሞች ላይም በደራሲነት እና በአዘጋጅነት እንድትሳተፍ አስችሏታል። በፅሐፍቶቹ የተጠነሰሱት በ1990 እ.አ.አ. ከማንችስተር ወደ ለንደን በተደረገ የባቡር ጉዞ ነበር።
ተጨማሪ ይዩ
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |