ጄተቨነራመየአኑራደፑረስሪ ላንካ የሚገኝ ጥንታዊ የቡዲስም ትልቅ ገዳምቤተ መቅደስ ነበር። በ270 ዓክልበ. በንጉስ መሃሴነ ተመሠረተ። እስከ 1157 ዓም ድረስ ቆመ።

ጄተቨነራመየ

ከእርሱ በፊት ትልቁ የጤራቫዳ ቡዲስም ተቋም አኑራደፑረ መሃቪሃረ ከ244 ዓክልበ. ጀምሮ ይኖር ነበር፤ በ80 ዓክልበ. ግን 300 መኖክሶች ከመሃቪሃረ ተገንጥለው ወደ አዲሱ አበየጊረ ተዛውረው አዲስ የቡዲስም ወገን ጀመሩ። የአበየጊሪ ጤራቫዳ ወገን ግን ከመሃያነ ቡዲስም ወገን ትምህርቶች ጋራ ተቀላቀለ።

የአኑራደፑረ መንግሥት ነገሥታት አደልዎን ለአበየጊሪ ወገን ያሳዩ ነበር። እንዲሁም መሃሴነ መሃቪሃረውን አጥፍቶ አዲስ ሦስተኛ ተቋም ጄተቨና በአኑራደፑረ ከተማ መሠረተ። ከዚህ ትንሽ በኋላ ግን ያው ንጉሥ ዳግመኛ መሃቪሃረውን አሠራ። ይሄ ሦስተኛው ተቋም ጄተቨና ደግሞ ከ270 እስከ 1157 ዓም ድረስ ቆመ።

በ1157 ዓም የአበየጊሪና የጄተቨና ተቋማት ሃራ ጤቆች ተብለው ያው ቪሃረ በንጉሥ ፩ ፐራክረመባሁ ትዕዛዝ ተዘጋና ሌሎቹ ሁለት ተቋማት ወደ መሃቪሃረ ተጨመሩ። ከ1157 ዓም ጀምሮ ጤራቫዳ ብቻ ተደገፈ።

ተቋሙ ያስተማረው በተለይ ለቡዲስም ተከታዮች የሚገቡት ጽሁፎችና ኑሮ ዘዴዎች በተመለከተ ነበር።