ዶሄ (ኮሪይኛ፦ 도해) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን ኖዕል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።

በጠቅላላ ለ57 ዓመታት (ምናልባት 1676-1619 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ አሃን ተከተለው።

1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ዶሄ ካደረጋቸው ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦

  • 1676 ዓክልበ. ግ. - ዳንጉን ኖዕል ዓረፈና አልጋ ወራሹ ልዑል ዶሄ ዳንጉን ሆኖ ነገሠ። አምስቱ ሚንስትሮች በ፲፪ ተራሮች መካከል የተቀደሠ ሥፍራ እንዲመርጡ አዘዛቸው፤ በዚያ የዛፍ ጣኦት ተሠራ። ዶሄ ደግሞ የተቀደሠ ቤተ መንግሥት ሠራ።
  • 1648 ዓክልበ. ግ. - የአገሩ ብርቅና ውድ ነገሮች በአንድ ታላቅ መግለጫ ታዩ።
ቀዳሚው
ኖዕል
ጆሰን ዳንጉን ተከታይ
አሃን

ዋቢ ምንጭ

ለማስተካከል