ድራኩንሱሊአሲስ
ድራኩሊኣሲስ, እዲሁም ጊኒ ዋርም በሽታ የሚባለው (GWD), በ guinea wormየሚተላለፍ ነው፡፡ [1] በ water fleas የተበከለ ውሀ የጠጣ ሰው በጊኒዋርም larva ይያዛል፡፡ [1] ሲጀምር ምንም ምልክት የለውም፡፡ [2] ከአንድ አመት በኋላ፣ ሴቷ ትል በቆዳ ላይ በምትፈጥረው ውሀ ያዘለ ቁስል ምክንያት ተጠቂው ሰው የማቃጠል ህመም ይሰማዋል፣ ይህም ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በታችኛው የሰውነት ክፍል ላይ ነው፡፡ [1] ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ትሉ ከቆዳ ውስጥ ይወጣል፡፡ [3] በዚህ ወቅትም መራመድና መስራት አዳጋች ይሆናል፡፡ [2] በሽታው ለሞት የመዳረጉ ሁኔታ ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ [1]
ድራኩንሱሊአሲስ | |
---|---|
Classification and external resources | |
የክብሪት እንጨት በመጠቀም ከእግር ላይ ጊኒ ዋርም ማውጣት | |
ICD-10 | B72 |
ICD-9 | 125.7 |
DiseasesDB | 3945 |
eMedicine | ped/616 |
Patient UK | ድራኩንሱሊአሲስ |
MeSH | D004320 |
ከእንስሳት መካከል በጊኒ ዋርም የሚጠቃው የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡ [2] ትሉ ከአንድ እስከ ሁለት ሚሊ ሜትር ስፋት ሲኖረው አንድ ትልቅ ሴት ትል ከ 60 እስከ 100 ሴንቲሜትር ትረዝማለች (ወንዱ አጭር ነው)፡፡ [1][2] ከሰው አካል ውጪ እንቁላሉ ለሶስት ሳምንታት ያህል ሊቆይ ይችላል፡፡ [4] ከዚህ በፊት በውሀ ውስጥ ቁንጫዎች መበላት አለባቸው፡፡ [1] በውሀ ቁንጫ ውስጥ ያለው ላርቫ ለአራት ወራት ያህል ሳይሞት ሊቆይ ይችላል፡፡ [4] በቦታው ላይ በሚቆዩ ሰዎች ላይ በሽታው በየአመቱ መከሰቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ [5] አብዛኛውን ጊዜ የበሽታው ምርመራ የሚካሄደው በምልክቶቹ ነው፡፡ [6]
መከላከሱ በበሽታው ቅድመ ምርመራና ሰውየው ትሎቹን ወደ መጠጥ ውሀ እንዳያሰራች በማድረግ ይሆናል፡፡ [1] ሌሎች ጥረቶች የሚያካትቱት፡- ንፁህ ውሀ አቅርቦት ወይም ንፁህ ላልሆነ ውሀ ማጣሪያ መጠቀምን ነው፡፡ [1] አብዛኛውን ጊዜ በጨርቅ ማጣራት በቂ ነው፡፡ [3] የተመረዘ ውሀ temefos ተብሎ በሚታወቀው ኬሚካል በመጨመር ላርቫውን መግደል ይቻላል፡፡[1] ለህመሙ ምንም አይነት መድሀኒት ወይም ክትባት የለም፡፡ [1] ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በቀስታ አንጨት በማንከባለል ትሉን ማውጣት ይቻላል፡፡ [2] በትሉ አማካኝነት የተፈጠረው ቁስል በባክቴሪያ ሊጠቃ ይችላል፡፡ [2] ትሉ ከወጣ በኋላም ህመሙ ለወራት ያህል ይዘልቃል፡፡ [2]
በ2013 በሽታውን የተመለከቱ 148 ጉዳዮች ሪፖርት ተደርገው ነበር፡፡[1] ይህ በ 1986 ከነበረው በ 3.5 ሚሊየን ቀንሷል፡፡ [2] በአፍሪካ በ 1980 ከነበረው 20 ሀገራት ቀንሶ 4 ብቻ ቀርተዋል፡፡ [1] ከዚህም ውስጥ በጣም የተጠቃችው ሀገር [South Sudan]]ናት፡፡ [1] ለመጀመሪያ ጊዜ የመጥፋት እድል ያለው የparasitic disease ነው፡፡[7] ጊኒ ዋርም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የነበረ በሽታ ነው፡፡ [2] ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 1550 በግብፃውያን ህክምና [[Ebers Papyrus] ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ [8] ደራኩኒሲሊሲስ የሚለው ስም የተገኘው ከ Latin ሲሆን "ስቃይ በትንሽ ደራጎኖች " የሚል ትርጉም አለው፡፡ [9] አውሮፓውያን ለመጀመሪያ ጊዜ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን በሽታውን ያዩት በ Guinea ባህር ዳርቻ West Africa ስለሆነ ስሙን "ጊኒ ዋርም" በለውታል፡፡ [8] ዝርያው ከጊኒ ዋርም ጋር የሚመሳሰል ሌሎች እንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ [10] ይህ በተጠቁ ሰዎች ላይ አልታየም፡፡[10] የተከፋፈለው በ neglected tropical diseaseነው ፡፡ [11]
References
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ "Dracunculiasis (guinea-worm disease) Fact sheet N°359 (Revised)". World Health Organization (March 2014). በ18 March 2014 የተወሰደ.
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ Greenaway, C (Feb 17, 2004). "Dracunculiasis (guinea worm disease).". CMAJ : Canadian Medical Association journal = journal de l'Association medicale canadienne 170 (4): 495–500. PMID 14970098.
- ^ ሀ ለ Cairncross, S; Tayeh, A ; Korkor, AS (Jun 2012). "Why is dracunculiasis eradication taking so long?". Trends in parasitology 28 (6): 225–30. doi:10.1016/j.pt.2012.03.003. PMID 22520367.
- ^ ሀ ለ Junghanss, Jeremy Farrar, Peter J. Hotez, Thomas (2013). Manson's tropical diseases. (23rd edition ed.). Oxford: Elsevier/Saunders. p. e62. ISBN 9780702053061. http://books.google.ca/books?id=GTjRAQAAQBAJ&pg=RA1-PA62.
- ^ "Parasites - Dracunculiasis (also known as Guinea Worm Disease) Eradication Program". CDC (November 22, 2013). በ19 March 2014 የተወሰደ.
- ^ Cook, Gordon (2009). Manson's tropical diseases. (22nd ed. ed.). [Edinburgh]: Saunders. p. 1506. ISBN 9781416044703. http://books.google.ca/books?id=CF2INI0O6l0C&pg=PA1506.
- ^ You must specify title = and url = when using {{cite web}}."". The Carter Center . Carter Center .
- ^ ሀ ለ You must specify title = and url = when using {{cite web}}.Tropical Medicine Central Resource . "". Uniformed Services University of the Health Sciences . በ2008-07-15 የተወሰደ.
- ^ Barry M (June 2007 ). "The tail end of guinea worm — global eradication without a drug or a vaccine ". N. Engl. J. Med. 356 (25 ): 2561–4 . doi:10.1056/NEJMp078089 . PMID 17582064 . Archived from the original on 2010-07-06 . https://web.archive.org/web/20100706035742/http://content.nejm.org/cgi/content/full/356/25/2561 በ2015-09-12 የተቃኘ.
- ^ ሀ ለ Junghanss, Jeremy Farrar, Peter J. Hotez, Thomas (2013). Manson's tropical diseases. (23rd edition ed.). Oxford: Elsevier/Saunders. p. 763. ISBN 9780702053061. http://books.google.ca/books?id=GTjRAQAAQBAJ&pg=PA763.
- ^ "Neglected Tropical Diseases" (June 6, 2011). በ28 November 2014 የተወሰደ.