ድልጫ
ድልጫ ህጻናት በክረምት ወራት የሚጫወቱት ጨዋታ ሲሆን፣ ዝናብ ከጣለ በኋላ የሰፈር ልጆች ተሰብስበው አንድ ምቹ ቦታ መርጠው ጭቃውን በማለስለስ ረጅም መስመር ይሰራሉ። ከዚያ ተራ በተራ ተንደርድረው መስመሩ ላይ በመንሸራተት በከፍተኛ ርዝመት የተንሸራተተ አሸናፊ ይሆናል። ይህ ጨዋታ ህጻናትን ለስራ የሚያነሳሳ፣ አካልዊ ጥንካሬን የሚያስተምርና ብሎም አብሮ መስራትን የሚያስተምር ነው።
ወላጆች የሚጠሉት የልጆቹ ልብስ በጭቃ ስለሚበላሽ ብቻ ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |