ዳሳሻዊነት
ዳሳሻዊነት ዕውቀት የሚመጣው ባብዛኛው ወይንም ሙሉ በሙሉ ከሥሜት ሕዋሳት ግንዛቤ ነው የሚል የፍልስፍና አይነት ነው። በሌላ አነጋገር ዕውቀት ከአመክንዮ ሳይሆን ከልምድ የሚነሳ ነው ይሚል አስተሳሰብ ነው።
በዚህ ፍልስፍና፣ ሰዎች ሲዎለዱ ባዶ ቅል ናቸው። ማለት በ አ ዕምሯቸው ምንም አይነት ዕውቀት የለም። ሆኖም ግን በዓለም ውስጥ በሚኖሩ ጊዜ፣ ከስሜት ህዋሳታቸው በሚያገኙት መረጃ ፣ ዕውቀት ይገነባሉ። ለምሳሌ አንድ ሕጻን ልጅ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ እሳት ቢመለከት፣ እንደሚያቃጥለው አያውቅም። እጁን ወድ እሳቱ ቢሰድ፣ እንደሚያቃጥል ያውቃል። ከዚህ ልምድ ተነስቶ እሳት ውሃን ያፈላል እሚል ድምዳሜ ላይ አይደርስም። ይልቁኑ አሁን፣ እሳት ውሃን ወደ እንፋሎት ሲቀይር በተደጋጋሚ ሲመለከት አዲስ ዕውቀት ይሰራል። ይህም እሳት ውሃን ወደ እንፋሎት እንደሚቀይር። በዚህ መልክ፣ ማናቸውም ዕውቀት የልማድ ውጤት እየሆነ ይሄዳል ይላል ዳሳሻዊነት።