ዲትር ባክማን
ዲትር ባክማን (17 ዲሴምበር 1940 እ.ኤ.አ. በባዝል ተወልዶ) የስዊዘርላንድ ጸሐፊና ጋዜጠኛ ነው።
ሕይወት
ለማስተካከልዲትር ባክማን «ጀርማናዊነት»ና ፍልስፍና አጠና እና በ1969 እ.ኤ.አ. ከዩኒቨርሲቴ ኦፍ ዙሪክ ተማረቀ። ጋዜጠኛ ሆኖ በመጀመርያ (ከ1970 እ.ኤ.አ.) የቬልትቮክ ምጽሔት አዘጋጅ ነበር፤ ከዚያ ታገስ አንጻይገር ምጽሔት አዘጋጅ ሆነ። በኋላ ላይኛ አዘጋጅ ለስዊስ ባሕላዊ ምጽሔት ዱ ሆነ።
ከ1975 እ.ኤ.አ. እና 1985 እ.ኤ.አ. መካከል የፕሮ ሄልቬቲያ ባሕላዊ ጉባኤ አባል ነበረ። ከ2000 እ.ኤ.አ. እስከ 2003 እ.ኤ.አ. ድረስ የኢስቲቱቶ ስቪጸሮ ዲ ሮማ (የሮማ ስዊስ ተቋም) አለቃ ነበረ። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በተለይ በጣልያን አገር ይኖራል።
ባክማን ደግሞ የስዊስ ጸሐፊዎችና ደራስያን ማሕበር እና የስዊስ ማተሚያ ማሕበር (VSP) አባል ነው።
ሽልማቶች
ለማስተካከል- 1984 እ.ኤ.አ. - የዙሪክ ጸሐፊዎች ሽልማት፣ አንድ ሰንበታዊ አማት በአርጋው ክፍላገር ተቀበለ።
- 2001 እ.ኤ.አ. - የግል ጽሑፎች ሽልማት፣ ከስዊስ ሺለር ተቋም
ሥራዎች
ለማስተካከል- ራብ (ልብ ወለድ) 1985 እ.ኤ.አ.
- ዞርገን ኢም ፓራዲስ (ጭንቀት በገነት) 1987 እ.ኤ.አ.
- ደር ኩርጸር አተም (ኣጭሩ ትንፋሽ) 1998 እ.ኤ.አ.
- ግሪምሰልስ ዛይት (የግሪምሰል ጊዜ) 2002 እ.ኤ.አ.
- ኡንተር ቲረን (በእንስሶች መካከል) 2010 እ.ኤ.አ.
ከነዚህ በላይ ብዙ ሌላ አይነት ጽሑፎች በየጊዜ እያቀረበ ነው።