ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት
ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት' በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ወላይታ አውራጃ በአስተዳዳሪነት በቆዩበት ጊዜ ብዙ የልማት ሥራዎችን አከናውነዋል።
ከሠሯቸው አበይት ሥራዎቻቸውም ፦
- ሰባቱንም ወረዳዎች የሚያገናኝ መንገድ አሰርተዋል።
- በሚሲዮናዊያን አማካኝነት የመጀመሪያውን የደቡብ ሆስፒታል አስገንብተዋል።
- ወላይታን ከምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገናኝና ፺ ሜትር ርዝመት ያለውን ታሪካዊውን የኦሞ ድልድይ አሠርተዋል።
- ወጣቱ ትርፍ ጊዜውን የሚያሳልፈበትን ወ.ወ.ክ.ማ. (የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር የወጣቶች መንደር ከዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት ጋር አሰርተዋል።
- በሶዶ ከተማ ዘመናዊ የገበያ አዳራሽ ከማሠራታቸው ነው።
- ከይርጋለም ቀጥሎ በደቡብ የመጀመሪያውን ከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ተማሪ ቤት አሠርተዋል።