እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን
(ከደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተዛወረ)
ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።
ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ፡፡
ዋቢ ምንጭ
ለማስተካከል- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊ ድርጅት፣ “ትንሣኤ፡ የሃያ አምስት ዓመታት መንፈሳዊ እርምጃ” (፲፱፻፶፱ ዓ/ም) ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት።