መለጠፊያ:ፖለቲካ


ዮናስ እሸቴ
ዮናስ እሸቴ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ ጋር
ዮናስ እሸቴ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ ጋር
የወጣቶች ፓርላማ አባል
የተወለዱት ሰኔ ፩፮ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.
አዲስ አበባኢትዮጵያ
የፖለቲካ ፓርቲ የህዝባዊ አንድነት ንቅናቄ ወይም UMP
ዜግነት ኢትዮ ፈረንሳዊ


ዮናስ እሸቴ ሰኔ ፩፮ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. በአዲስ አበባ የተወለደ የኢትዮ-ፈረንሳይ የፖለቲካ ሰው[1] እንዲሁም የፖለቲካና የኮምኒኬሽን አማካሪ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የህዝባዊ አንድነት ንቅናቄ የፈረንሳይ ቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባልና የፓርቲው የክልላዊ የወጣቶች ተጠሪ ነው[2]

የግል ህይወት ለማስተካከል

ዮናስ ወላጆቹ የጎንደር ተወላጅ ሴናተር ካሳ ናኩቶላብ የልጅ ልጅ ሲሆን ተወልዶ እስከ ጉልምስናው ድረስ ያደገው ግን በመዲናዋ አዲስ አበባ ነው። እድሜው ለጉልምሰና ሲደርስ ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ስትራስበርግ ከተማ ትምህርቱን አጠናቋል። ዮናስ አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ እንግሊዝኛና ስፓኒሽ ቋንቋ በማቀላጠፍ ይናገራል።

ፖለቲካ ህይወት ለማስተካከል

ክ፪፻፰ እስከ ፳፩፱ የስትራስበርግ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ኮሚሽን በመመረጥ የተማሪዎች ተወካይ ነበረ። ፳፻፪ ዓ.ም. የሬፐብሊካን ፓርቲ በመቀላቀል የክልል የወጣቶች ተጠሪ[3] በመሆን የኒኮላ ሳርኮዚ ፓርቲን ያገለግላል። ከ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት ወይዘሮ ሶፊ ሮፍሪች የፖለቲካና የኮሚኒኬሽን አማካሪ በመሆን ያገለግላል።

ህዳር ፩፫ ቀን የአልሳስ ክልል የወጣቶች ፓርላማ አባል በመሆን ተመርጧል።

  1. ^ https://soundcloud.com/julienrino/yonas-eshete
  2. ^ http://www.purepeople.com/media/pierre-sarkozy-le-31-mars-2012-a-paris_m824757
  3. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2015-03-26. በ2015-01-22 የተወሰደ.