የጋዝ ብርሃን ማድረግ በዘመናዊ ምዕራባውያን ፖሊቲካ ዘይቤ ሲሆን በአጠቃላይ «ማታለል» ማለት ነው።

ተዋናይት ኢንግርድ በርግማን ስትታለል በ1936 ዓም ፊልም «የጋዝ ብርሃን»

በተለይ «የጋዝ ብርሃን ማድረግ» አንድ ድርጊት አልተደረገም ብሎ ለማስመስል ማለት ነው። ተደረገ እንጂ የሚሉ ሁሉ ከዚያ እንደ እብዶች ወይም እንደ ተሳቱ ደግሞ ማስመስል ነው።

የዘይቤው መነሻ ከአንድ 1930 ዓም ድራማ በእንግሊዝኛ «የጋዝ ብርሃን» መጣ። በዚህ ድራማ (በኋላም በ1936 ዓም ፊልም)፣ አንድ ውሸታም ባል ሚስቱን በጣም ረቂቅ በሆነ በጋዝ ብርሃን ያታላታል።