የጋዜጠኛ መሃመድ ስራጅ አጭር የህይወት ታሪክ
• ሙሉ ስም ከነአያት፡___መሃመድ ስራጅ ዋበላ • እምነት፡- ሙስሊም • ዕድሜ፡__38 • ጾታ፡__ወንድ • ዜግነት፡- ኢትዮጵያዊ • አሁን የሚሰራው ሥራ (መስሪያ ቤት)፡- የማስታወቂያ ባለሙያ፤ደራሲ፤የማህበረሰብ አንቂና ጋዜጠኛ ሲሆን በአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ በዋና ስራ አስኪያጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡ የት/ ደረጃ፡- የመጀመሪያ ድግሪ በቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ፤በሁለተኛ ድግሪ በማህበረሰብ ጥናት (Sociology) በአሁን ሰአት ደግሞ በሚችጋን ዩኒቨርሲቲ Leadership and Management (Leading People and Teams Specialization) Masters Program From University of Michigan.
የስራ ልምድ፡_ ከ19/97 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኗ ሰአት ድረስ 18 አመት በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ከባለሙያ እስከ ከፍተኛ ሃላፊነት፤በግል ስራ ድርጅት አስተዳደር፤በጋዜጠኝነትና በማህበረሰብ አንቂነት እየሰራ ሲሆን በአሁን ሰአትም በአለም አቀፍ ተደማጭነት ባለው ተወዳጅና ተመራጭ የራዲዮ ጣቢያ አዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ራዲዮ በስራ አስኪያጅነት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በአመራሩም በሃገራችን ካሉ ሚዲያዎች በዚሁ አመት በኢትጵ ብዙሃን መገናኛ ተሸላሚ እንዲሆን አድርጓል፡፡ • ጋዜጠኛ መሃመድ ስራጅ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሃገሩን በተሰማራባቸው ዘርፎች በታማኝነት፤በቅንነትና ያለ አድሎ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ በጋዜጠኝነትና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ከ18 አመታት በላይ ያገለገለ ሲሆን በዋናነት ከሰራባቸው የሚደያ ተቋማቶች መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን፤በፋና፤ በዋልታ፤በኢ.ቢ.ኤስ፤በኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1፤በአሐዱ ኤፍ.ኤም.94.3፤በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአዋሽ 90.7 ኤፍ.ኤም በስራ አስኪያጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡ • ጋዜጠኛ መሃመድ ሃገሩን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በተለያዩ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ሰርቷል፤በማህበረሰብ አንቂነት፤በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች፤ከግለሰብ አስከ ክልልና ብሔሮች መካከል በእርቅና በሰላም፤በባህልና በቱሪዝም፤በሐይማኖት አብሮነት፤በዲሞክራሲና ኢኮኖሚ ግንባታ፤በስራ ባህል መዳበር፤
• የኢትዮጵያ ኩላሊት ህሙማን እጥበት ማህበርን በመመስረት፤ገንዘብ በማሰባሰብና በመደገፍ፣ የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎትን በመደገፍና ደም በማሰባሰብ፣ በጎዳና ላይ ህጻናቶች በበርካታ የህብረተሰባዊ ድጋፍ አገልግሎቶች ላይ ተሳትፎ በማድረግ እና በማህበራዊ ጉዳዮች በመንቀሳቀስ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተለይ የህጻናት ማሳደጊያዎችን ገቢ በማሰባሰብ፤በመደገፍና በማስተባበር የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመመገብና ከሱሰኝነት እንዲላቀቁ በማድረግ፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በጋብቻ እና በኢንተርፕርነሮች ዘርፎች ባለሞያዎችን በማስተባበር በነጻ ስልጠና ለተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች እየሰጠም እያሰጠም ይገኛል፡፡
• ጋዜጠኛና ደራሲ መሃመድ ስራጅ በተለያየ ጊዜያት ከ500,000 ሰው በላይ ጊዜያዊ የስራ እድል ፈጠራ፤በአወንታዊና ሀገራዊ አስተሳሰብ፤በተለያዩ ሃገር በቀል ፕሮጀክቶች፤በሀገርና በስብእና ገጽታ ግንባታ፤በህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰብ፤በ6ተኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ፤በሰሜኑ አካባቢ በተከሰተው ጦርነት ከገቢ ማሰባሰብ እስከ የጦር ዘገባ፤
• ለተከታታይ 10 አመታት በተለያዩ በክልልና በማህበረሰብ ራዲዮ፤በሚኒ-ሚዲያና በተለያዩ ክበባት በተግባቦት፤በመሰራዊ ጋዜጠኝነት፤በራስ ማሰተዳደር እና በሌሎች የህይወትና የስራ ክህሎቶች ከ1,5000 ሰው በላይ በነጻ ስልጠና በመስጠት፤በኮቪድ-19 የግንዛቤ ፈጠራና ገቢ ማሰባሰብ፤የየክልል ልማት ማህበሮች ገቢ ማሰባሰብ፤በህገ-ወጥ ስደት፤በአረንጓዴ አሻራ፤በዲፕሎማሲ፤በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ፤በሃገራዊ መግባባትና የተለያዩ የአስተሳሰብ ከፍታን የሚያሳዩ ሃገር የሚያሻግሩ በራሱ ወጪ ስድስት(6)ታትመው ለንባብ የበቁ መጽሐፎች ‹‹ከሰማይ ውስጥ››፤‹‹ከፍታ››፤ ‹‹ጋብቻና ፍቅር››፤‹‹መሪ››፤‹‹ይመለከተኛል ኢትዮጵያ›› የተሰኙ መጽሃፎችን ለሃገሩ አንባቢዎች ያበረከተና ሌሎች በአሁን ሰአት ለህትመት የተዘጋጁ ከስምንት (8) በላይ እጅግ ትውልድን የሚቀይሩ አወንታዊ አስተሳሰብን፤የስራ ባህልን፤የቁጠባ ባህልን፤የንባብ ባህልንና የአብሮነት እሴትን የሚያዳብሩና ለጥናትና ምርምር መነሻ የሚሆኑ ዝግጅትና አርትኦት ስራቸው ጥንቅቅ ያሉ አእምሮን የሚለሙ መጽሃፎቶች በእጁ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለነዚህም ስራዎቹ ምስክርነት መንግታዊና መንግታዊ ካልሆኑ ተቋማት ከመቶ ሰማንያ (180) በላይ የምስጋናና የምስክር ወረቀቶች በማህደሩ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ500,000 (ከአምስት መቶ ሺ) በላይ ተከታይ ባለው የግል ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም አነቃቂና ሃገራዊ ሃሳቦችን በማንሳት ማህበረሰቡን በሃገር ፍቅር፤በመልካም ስነ ምግባር በማሳወቅ፤በመቀስቀስና ተአማኝ መረጃ በመስጠት ሃገሩ በፈለገችው ቦታዎች ሁሉ በፍትሃዊነት፤በታማኝነትና በልማታዊ አስተሳሰብ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሃገሩን በቁርጠኝነት እያገለገለ ይገኛል፡፡
• ጋዜጠኛና ደራሲ መሃመድ ስራጅ በአሁን ሰአትም በአዋሽ 90.7 ኤፍ.ኤም ከስራ አስኪያጅነት በተጨማሪ ተወዳጅና ትውልድ ገንቢ የሆኑ ‹‹ከአባይ ጓዳ››፤ ‹‹ይመለከተኛል ኢትዮጵያ››፤ ‹‹አዋሽ ስፔሻል›› ፤ “አዋሽ ወቅታዊ”ና ሌሎችንም ፕሮግራሞችን በዋና አዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡