ክፍል ፬ ለማስተካከል

የመጀመሪያወቹ ሶስት ክፍሎች ያለምንም ችግር በራሳቸው አንድ የተሟላ ጽሁፍ ይወጣቸዋል፣ ከዚህ አንጻር አራተኛው ክፍል የኒህ የሶስቱ አካል ይሁን እራሱን የቻለ ክፍል ይሁን የሚለው በተመራማሪወች ዘንድ ክርክር አለ። በዚህ ክፍል ዞራስተር አርጅቶ እናገኘዋለን። እንደድሮው ከተራራው ወርዶ ማስተማር አቁሞ የሚፈልጉት ሰወች ተራራው ድርስ መጥተው ትምህርት ሲወስዱ እናነባለን። ዞራስተር ከትልልቅ ሰወች ጋር በመገናኘት እራሱን በኒህ ሰወች ይከባል፣ ምግብንም ከነሱ ጋር ይካፈላል፡፡ እነዚህ ታላላቅ ሰወች፡ የግራና የቀኙ ንጉሶች፣ የአረጀው ምትሃተኛ፣ የሮማው ፓፓ፣ ፈቃደኛው ለማኝና ጥላው፣ ንጹህ አዕምሮ፣ በጣም ፉንጋው ሰው ናቸው። ሁሉም በአዕምሮአቸው ትክክል ነው ብለው የተቀበሉት ነገር ትክክል ሳይሆን (አምላክ፣ እውነት፣ ልብ) ተጣሞባቸው ስላገኙ፣ ሆኖም ግን ከዚህ በመነሳት ውሳኔ ላይ መድረስ አቅቷቸው ተስፋ የቆረጡ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ድሮ ይሰሩት የነበረውን ስራ መስራት አቅቷቸው የድሮው ስራቸው ተዋናይ/ገጸ ባህርይ ወደ መሆን የወረዱ ነበሩ። ለነዚህ ሰወች ሃዘን ሊገባው የነበረው ዞራስተር ከሃዘኑ ጋር ትንቅንቅ በመፍጠር ሃዘኑን ማሸነፍ እንዳለበት ያሳያል።

[...] "የመጨረሻው ጥፋቴ ምን ይሆን?" ብሎ እራሱን ጠየቀ
ከዚህ በኋላ ዞራስተር ወደ ራሱ አዕምሮ አተኮረ፣ ከትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀምጦም አንሰላሰለ። በድንገት ተስተካክሎ ተቀመጠ፣ መለሰም፦
"ለታላላቆቹ ሰወች ከንፈር መምጠጥ! " በዚህ ጊዜ ፊቱ ወደ ንሐስ ተቀየረ

ከዚህ በኋላ በዚህ ክፍል ዞራስተር እንደ አዲስ ሰው ተቀየረ፣

[...]"አንበሳውም መጥቷል፣ ልጆቸም ተቃርበዋል፣ ዞራስተርም በስሏል፣ ሰዓቴም ተቃርቧል፦ ጎሄ ቀደደ፣ ቀኔ ጀመረ፣ ተነሳ! ተነሳ! አንት ድንቅ ቀትር!"
እንዲህ በመናገር ከድቅድቅ ተራራ መካከል እየተፈናጠቀች እንደምትወጣ የንጋት ጮራ እያብረቀረቀ ዞራስተር ዋሻውን ለቆ ወጣ።