አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

 8 መካከለኛ ጭልፋ (800 ግራም) በትልቁ የተከተፈ ተላፒያ ዓሣ
 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቲማቲም
 3 ፍሬው ወጥቶ የተከተፈ ቃርያ
 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
 4 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
 4 መካከለኛ ጭልፋ (250 ግራም) የተቀቀለ ሩዝ
 ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
 ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት

1. ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላት፤
2. ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
3. የቲማቲም ድልህ ጨምሮ ማዋሃድ፤
4. የተከተፈውን ቲማቲም መጨመርና በደንብ እስኪበስል ማንተክተክ፤
5. ከላይ በተሠራው ሶስ ዓሣውን፣ ቁንዶ በርበሬና ጨውን ጨምሮ ማማሰል፤
6. ሲበስል ቃርያ ነስንሶ ከሩዙ ጋር ቀላቅሎ ማቅረብ፡፡