የኦዞን ንጣፍ በመሬት ከባቢ አየር ውስጥ የሚገኝ ንጣፍ ሲሆን በአንፃራዊ ሁኔታ ከፍተኛ መጠን ያለው ኦዞን (O3) የያዘ ነው። ይህ ንጣፍ ከ97 እስከ 99 በመቶ የሚሆነውን ባለከፍተኛ ድግግሞሽ አልትራቫዮሌት ጨረር የመምጠጥ አቅም አለው።