የኤልያስ ራዕይ በጥንት ለአይሁዶችና ለክርስቲያኖች የታወቀ ትንቢት ነው። ይህ ትንቢት በ2 የተለያዩ መጽሐፍት ይገኛል። እነርሱም የዕብራይስጥ አይሁድ ትርጉም (ሠፈር ኤሊያሁ)፣ እና በቅብጢኛ የተጻፈው በክርስቱያኖች የተዘጋጀ ትርጉም ናቸው። እነዚህ ብርቅ ጽሑፎች በሰፊ አልታወቁምና መቸም ቀኖናዊ ሳይቆጠሩ ከአዋልድም መጻሕፍት ውጭ ቀሩ። እያንዳንዱ ትርጉም የነቢይ ኤልያስ ስም ስላለበት፣ ለዚህ ነው «የኤልያስ ራዕይ» የተባለው እንጂ በኤልያስ እራሱ እንደ ተጻፈ አይመስልም ወይም አይልም። ዛሬ ያሉኑ ቅጂዎች በሙሉ ያልሆኑ ፍርስራሾች በመሆናቸው፣ ይዞታው በከፊል ብቻ ይታወቃል።

ጽሑፉ ለብዙ ቀድሞ የቤተ ክርስቲያን አበው ይታወቅና ይጠቀስ ነበር። ኦሪጌኔስ (220 ዓ.ም. አካባቢ) እና ሌሎች አበው እንደ ጻፉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ጽሑፍ በ1 ቆሮ. 2፡9 የጠቀሱ ነበር፦

«ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው»።

እንዲሁም የሳላሚስ ኤጲስ ቆጶስ አጲፋንዮስ ዘሳላሚስ (375 ዓ.ም. ግድም) እንዳሉ፣ ጳውሎስ ደግሞ የኤልያስ ራዕይን በኤፌ. 5፡14 ጠቅሰዋል፦

«አንተ የምትተኛ ንቃ፣ ከሙታንም ተነሣ፣ ክርስቶስም ያበራልሃል።»

አሁን የሚታወቁት ሁለት ልዩ ልዩ የኤልያስ ራዕይ ትርጉሞች እጅግ የተዛቡ ይመስላል።

የአይሁድ (ዕብራይስጥ) ሠፈር ኤሊያሁ ለማስተካከል

የዕብራይስጥ ቅጂ ብዙ ጊዜ እንደ ተጨመረበት ወይም እንደ ተጎደለበት ግልጽ ነው። ነቢዩ ኤልያስ የኖረው በ860 ዓክልበ. ግድም እንደ ነበር ይታስባል። ነገር ግን ከዚህ በኋላ የኖሩ ሰዎች ጥቅሶችን በሰፊ ጨመሩ። ለምሳሌ ነቢዩ ዘካርያስ (520 ዓክልበ. ግድም) ይጠቀሳል። ከዚህ በላይ በ1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የኖሩ የአይሁድ ረቢዎች ጥቅሶች ይሠጣሉ።

በዚህ ትርጉም ያለው ትምህርት እንዲሁ ነው። መልአኩ ሚካኤል መጀመርያ ራዕዩን ለኤልያስ በደብረ ቀርሜሎስ ገለጸው። ይህም ስለ መጨረሻ ዘመን ይነካል። በመጨረሻ ዘመናት ከፋርስና ከሮማ ነገሥታት መካከል ትግል ይነሣል። በዚህ ትግል የሮማ ነገሥታት አይችሉበትም። በመጨረሻ ግን ክፉ ንጉሥ በሮማ ይነሣል። እርሱ ሐሣዊ ምልክት ያሳያልና የእስራኤልን ልጆች ይገድላል። ደብረ ጽዮንን እንኳን ያቃጥላል። የሁለቱ ነገሥታት ታላቅ ሠራዊቶች ለአንድ ታላቅ ውጊያ ይሠልፋሉ፤ በጠቅላላ ከ300,000 በላይ ወታደሮች ይሆናሉ። ነገር ግን አሁን መሢሕ ይደርሳል። ሠራዊቶቹ በሽብር ተይዘው የአለምን አገራት ይገጽሣቸውና መሢሑ ለ40 አመታት እስራኤልን በመንግሥት ያስደስታታል።

ከዚህ ጊዜያዊ መንግሥት በኋላ፣ የጉግማንጉግ ሃያላት ይመልሳሉና ኢየሩሳሌምን እንደገና ይከብባሉ። ዳሩ ግን መሢሑ ድንገት ተመልሶ ከመላእክቱ ጋር በሙሉ ያጥፋቸዋል። ከዚህ ጥፋት በኋላ የሙታን ትንሳኤዕለተ ደይንየእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት ይቀጥላሉ። በዚህ መንግሥት፣ ሕዝቦች ሁሉ ሀብት ወደ አዲስ ኢየሩሳሌም ያመጣሉ።

የቅብጥ ትርጉም ለማስተካከል

የቅብጢ ትርጉም ደግሞ በጣም ተዛብቷል። ከዕብራይስጡም ትርጉም በፍጹም ይለያል። በዚህ ውስጥ፣ የሚታግሉ ተቃዋሚ ሃያላት አሦርግብጽ ናችው። ክፉ ንጉሥ ከምእራብ ይነሣልና ግብጽን ያባብላል። ስለዚህ የግብጽ ኃይል ይወድቃልና በሥፍራው ፋርስ ይነሣል። ፋርስና አሦር በሚታግሉበት ዘመን፣ ሌላ ሕገ ወጥ መሪ ይታያል፤ እሱም ሐሣዌ መሢህ ነው። የውሸት ተአምርም ያበዛል። ኤልያስና ሄኖክ ተነሥተው ይገጽሡታል። ስለዚህ እሱ ምእመናኑን ያሠቃያል። በመጨረሻ ግን ክርስቶስ መላዕክቱን ልኮ ምድርን በእሳት ያጠፋሉ። ወዲያው ዕለተ ደይንና የክርስቶስ ጊዜያዊ መንግሥት ለ1000 አመት ይቀጥላል።

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል