በኢትዮጵያ የወይን ምርትን አጀማመር ወደኋላ ስናየው በመጀመሪያው ሺህ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ነው። [1] የታሪክ ጸሃፊው ምሁሩ ሪቻርድ ፓንክረስት የአክሱማውያን ወይን ጠጅ ቀደምት ማጣቀሻዎች በ 4 ኛው ክፍለ ዘመን ገዥ ኢዛና ካቆሙት የድንጋይ ሃውልት ውስጥ በአንዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል ። የ አክሱማውያንን የ ወይን ማልማት ጥበብ በአክሱም በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቆመው ታላቁ የአክሱም ሀውልት መሰረት ላይ የተቀረጹ ምስሎችም ይመሰክራሉ። [2] ባህላዊው የማር ወይን ጠጅ ከጥንት ጀምሮ በሰፊው ተወዳጅነት ያገኘ ነበር።

ጠጅ፣ የኢትዮጵያ ማር ወይን

የአሁኑ የወይን ማልማት ጥበብ በኢትዮጵያ የተጀመረው በ1956 በአዋሽ ወይን ፋብሪካ በስራ ፈጣሪዎቹ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ እና ራስ መስፍን ስለሺ ነው። እ.ኤ.አ. በ 2014 የአዋሽ ወይን ፋብሪካ 10 ሚሊዮን ጠርሙሶች አመታዊ ምርት ነበረው አብዛኛዎቹ ደሞ በአገር ውስጥ ነበር የተሸጡት። [1] እ.ኤ.አ. በ 2014 የፈረንሳይ መጠጥ ኮርፖሬሽን ካስቴል በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ዝዋይ አቅራቢያ ባለው 120 ሄክታር መሬት ላይ በርካታ የወይን ዝርያዎች ማምረት ጀመረ። እ.ኤ.አ. በ 2013 አመታዊ ምርቱ 3 ሚሊዮን ጠርሙሶች ነበር ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት በዋናነት ወደ ቻይና ተልከዋል። [2]

በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያለው የአየር ንብረት እና የመሬት አቀማመጥ ሁኔታዎች ለወይን ማልማት ተስማሚ ያደርጉታል። አመታዊ የዝናብ መጠን 650 ሚሜ አካባቢ ፣ የሙቀት መጠኑ በአማካይ 25 ዲግሪ ሴልሺየስ በዓመት እና ክልሉ በአሸዋማ አፈር የተሞላ ነው ይህ ደሞ ለወይን ምርት በጣም ተስማሚ ሁኔታዎች ናቸው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከምድር ወገብ ጋር ባላት ቅርበት ምክንያት በአመት ሁለት ምርት መሰብሰብ ይቻላል። [1] የኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች ምዕራባዊ ተዳፋት የሜዲትራኒያን የአየር ንብረት ስላላቸው ለወይን ማብቀል በጣም ምቹ ናቸው።

ማጣቀሻዎች

ለማስተካከል