የአፍሪካ ፈንግል ወይም እንቅልፍ የለሽ[1] የእንስሳትና የሌሎች እንስሳት ጥገኛ በሽታ ነው። መንስኤው በየፈንግል ብሩሲ ዝርያ ጥገኛ ህዋስ አማካኝነት ነው።[2] ሰዎችን የሚያጠቁ ሁለት አይነት ናቸው፣ ፈንግል ብሩሲ ጋምቢነስ (ቲ.ቢ.ጂ) እና ፈንግል ብሩሲ ሮዲሲንስ (ቲ.ቢ.አር.).[1] ቲ.ቢ.ጂ በሽታው ከተገኘባቸው ለ98% በላይ መንስኤ ሆኖ ተገኝቶአል።[1] ሁሉም ሚተላለፉት በተመረዘ የቆላ ዝንብ አማካኝነት ነው። በአብዛኛው በገጠር ቦታዎች የተለመዱ ናቸው።[1]

የአፍሪካ ፈንግል በሽታ
Classification and external resources

የፈንግል ቅርጾች በ lደም ጠብታ
ICD-10 B56
ICD-9 086.5
DiseasesDB 29277 13400
MedlinePlus 001362
eMedicine med/2140
Patient UK የአፍሪካ ፈንግል በሽታ
MeSH D014353

በመጀመሪያ፣ በበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ማሳከክ፣ እና የመገጣጠሚያ ህመም ስሜት ናቸው።[1] ይህም የሚጀመረው በተነከሱ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። [3] ከሳምንታትና ከወራት በኋላ የሁለተኛ ደረጃው ማቃዠት፣ መደንዘዝ፣ መዘባራቅና የእንቅልፍ ችግር በማስከተል ይጀምራል።[1][3] ምርመራው በደም ጠብታ ወይም በፍርንትት ፈሳሽ ውስጥ ጥገኛ ተህዋስያኑን በመፈለግ ይጀምራል። [3] የሸፊትነክ ቀዳዳ የበሽታውን የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ልዩነቱን ለመንገር ይፈለጋል።[3]

አሰቃቂውን በሽታ ለመከላከል ለአደጋው ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች የቲ.ቢ.ጂ የደም ምርመራ ማካሄድን ያካትታል።[1] በሽታው ገና እንደጀመረ ማለትም በስርአተ ነርብ ላይ ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት ከታወቀ በሽታውን ማዳን ቀላል ነው።[1] የመጀመሪያ ደረጃውን ለማከም ፔንታማይዲን ወይም ሱራሚን መድሀኒቶችን መጠቀም ነው።[1] የሁለተኛ ደረጃውን ለማከም ኢፍሎርንቲን ወይም ኒፉርቲሞክእና ኢፍሎርንቲን ቅልቅል ለቲ.ቢ.ጂ ይይዛል።[3] ምንም እንኳን ሜላርስፕሮል ለሁሉም ቢሰራም ፣ ከፍተኛ የጎንዮሽ ጉዳት ስላለው በተለይ ለ ቲ.ቢ.አር ያገለግላል።[1]

በሽታው ከሰሀራ በታች ባሉ በተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ይከሰታል፣ በ36 ሀገራት ውስጥ የሚገኙ 70 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአደጋ ላይ ናቸው።[4] በ2010 ለ9000 ሞት መንስኤ ሲሆን ይህም ቁጥር ከ1990 ማለትም 34,000 ከነበረው የቀነሰ ነው።[5] በ2012 ውስጥ አዲስ ከተያዙት 7000 ህመምተኞች ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በግምት 30,000 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።[1] ከነዚህ ህሙማን ውስጥ ከ80% የሚበልጠው በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ ነው።[1] በቅርብ ታሪክ ውስጥ ሶስት ዋና ዋና ወረርሽኞች ተነስተዋል፤ አንዱ ከ1896 እስከ 1906 እ.ኤ.አ. በዋናነት ዩጋንዳ ውስጥና በኮንጎ ቤዝንና ሁለቱ ደግሞ በበርካታ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ የተከሰቱ ሲሆን ይኸውም በ1920ና 1970 እ.ኤ.አ. የተከሰቱት ናቸው።[1] ላሞች እና ሌሎች እንስሳት በሽታውን ሊሸከሙ ይችላሉ፣ እናም በበሽታው ሊያዙ ይችላሉ።[1]

ማጣቀሻዎች

ለማስተካከል
  1. ^ (እንግሊዝኛ) WHO Media centre (June 2013). Fact sheet N°259: Trypanosomiasis, Human African (sleeping sickness). http://www.who.int/mediacentre/factsheets/fs259/en/. 
  2. ^ (እንግሊዝኛ) Medline Plus Encyclopedia - Sleeping sickness
  3. ^ (እንግሊዝኛ) Kennedy, PG (2013 Feb). "Clinical features, diagnosis, and treatment of human African trypanosomiasis (sleeping sickness).". Lancet neurology 12 (2): 186-94. PMID 23260189. 
  4. ^ (እንግሊዝኛ) Simarro PP, Cecchi G, Franco JR, Paone M, Diarra A, Ruiz-Postigo JA, Fèvre EM, Mattioli RC, Jannin JG (2012). "Estimating and Mapping the Population at Risk of Sleeping Sickness". PLoS Negl Trop Dis 6 (10): e1859. doi:10.1371/journal.pntd.0001859. 
  5. ^ (እንግሊዝኛ) Lozano, R (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010.". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604.