የአይሻል ጦርነት በደጃዝማች ካሳ ሃይሉ (ዓፄ ቴዎድሮስ ከመባላቸው በፊት) እና በራስ አሊ መካከል የተደረገ በደም የጨቀየ ጦርነት ነው። ድሉ ለደጃዝማች ካሳ ሆኖ የዘመነ መሳፍንት እና የየጁ ኃይልን ለመጨረሻ ጊዜ የሰበረ ጦርነት ነበር። ራስ አሊ በወቅቱ የካሳን ጦር ተመልክተው ፦ «መልእክተኛ እንዳንለው በዛ፣ ጦረኛ እንዳንለው አነሰ» ብለው እንደተሳለቁ በታሪክ ይዘገባል።

የአይሻል ጦርነት መነሻ

ለማስተካከል

ደጃዝማች ካሳ ሃይሉ በሸፈተ ጊዜ፣ ራስ አሊና እና እናቱ እቴጌ መነን ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያ መሪዎች ነበሩ። ስለሆነም ሃይላቸውን ሊጋራ እሚገዳደረውን፣ ሽፍታውን ካሳን በሃይል ለማንበርከክ ይፈልጉ ነበር። ሆኖም ለዚህ ተግባር ከአሊ የተላኩትን ደጃዝማች ብሩ ጎሹንብሩ አሊጋዝንና በለውን ሁሉንም ካሳ ስላሸነፈ፤ ራስ አሊ እጅግ ተቆጥቶ፣ በርሱ በራሱ በሚመራ ሠራዊት ሊዎጋው ፈለገ።

እስከዚህ ጊዜ ድረስ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ በሁለቱ ሃይሎች እሚካሄደውን ውጊያ ትኩረት ሰጥቶት አልተከታተለውም ነበር። ሆኖም ራስ አሊ እጅግ በመበሳጨቱ እና ይህ መጪው ጦርነት የአገሪቱን ሁኔታ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወስናል የሚል ወሬ በጣም ስለተናፈሰ፣ አብዛኛ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ሕዝብ የጦርነቱን ዜና ይከታተለው ነበር።

የጦርነቱ ሁኔታ

ለማስተካከል

ስለሆነም ራስ አሊም፣ ደጃች ካሳም በከፍተኛ ዝግጅት ሰኔ 23, 1845 ዓ.ም. በአይሻል፣ ምስራቅ ጎጃም ተገናኙ። በጊዜው የነበረው የእንግሊዙ ሚሲዮን ሄንሪ ስተርን ስለ ውጊያው ሲጽፍ [1] :

የሁለቱም ሠራዊት በከፍተኛ ጀብዱዎች ተዋጉ። የካሳ ሠራዊት በ[የጁ] እና በጌምድር ፈረሰኞች እየተሸነፉ ተበተኑ።  ሆኖም ወደኋላ የሚያፈገፍገው ካሳ ለማስመሰል እንጅ የእውነት አልነበረም። ባለ ድሎቹ፣ እነ ራስ አሊ በከፍተኛ ወኔ፣  በካሳ ሠራዊት ላይ ሽብርና ሞት እያዘነቡ ወደ ፊት ገፉ። የጠላታቸውን ብልጣብልጥነት አልተገነዘቡም ነበርና። አንድ ቁጥቋጦ እና ዛፍ የበዛበት ቦታ ሲደርሱ በየዛፉ ላይ የተንጠለጠሉ መስታውቶች  ተከሰቱባቸውና የፀሐይን ብርሃን ቦግ ቦግ እያረገ ሲያብረቀርቅባቸው፣ ፈረሶቻቸው ቆሙ። ቀጥሎም በተለያየ አቅጣጫ፣ የአካባቢው አፈር፣ ከውስጥ ተቦጥቡጦ ተቆፍሮ ነበርና፣ እንደ መዓት እየተደረመሰ ቦይ ሲሆን በመተት  የሚያምኑት  የጁዎች  ስራው የየጋኔኖች እና  የዕርኩስ መናፍስት መስሎ ታያቸው።  የአሊ ሠራዊት በግርምትና በፍርሃት በሚርዱበት በስተወዲያው ካሳ ከማፈግፈጉ ዞሮ  ወታደሮቹን በመምራት የአሊን የደነገጠ ሠራዊት ፈጀ።  [ራስ አሊም ተሸንፈው ስደተኛ ሆኑ]።

የጦርነቱ ፋይዳ

ለማስተካከል

በአይሻል ጦርነት ዘመነ መሳፍንት አበቃ።

  1. ^ stern, henry (1868) (in english). The Captive Missionary: Being an Account of the Country and People of Abyssinia. Embracing a Narrative of King Theodore's Life, and His Treatment of Political and Religious Missions. Cassel, Petter & Galpin. pp. 13. https://books.google.com/books?id=xStDAAAAcAAJ&lpg=PA13&ots=CJNmgYALEW&dq=aishal%20battle&pg=PA13#v=onepage&q=aishal%20battle&f=false.