የኅልውና ቀውስ የምንለው አንድ ግለሰብ በህይወት ጎዳናው ላይ በድንገት ቆም ብሎ በአጠቃላይ የህይወቱ መሰረቶች ላይ ጥያቄ ሲያቀርብ ነው፡- ለምሳሌ " ህይወቴ ትርጉም፣ ዋጋ ወይም አላማ አለው ወይ?" ብሎ ሲጠይቅ። ይህ ጉዳይ በኅልውነት ፍልስፍና ከፍተኛ ቦት ተሰጥቶት የሚጠና ነው።

የኅልውና ቀውስ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ባንድ ግለሰብ ህይወት ውስጥ ክፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክንውኖች ሲፈጸሙ ነው፣ ለምሳሌ ያልን እንደሆን

  • በአለም ውስጥ ብቻየን ነኝ ብሎ ከማሰብ
  • አንድ ግለሰብ በርግጥም መሞቱ የማይቀር መሆኑን በርግጥ ሲረዳ
  • አንድ ሰው ህይወቱ ትርጉም ሆነ አላማ እንደሌለው ሲገነዘብ
  • አንድ ሰው ሙሉ ነጻነት እንዳለው ሲረዳ፣ ሃላፊነቱንም በዛው ልክ ሲቀበል ወይም ሲክድ
  • እጅግ አስደሳች ወይም እጅግ ጎጂ የሆነ ጉዳይ በግለሰብ ላይ ሲደርስ
  • በጋብቻ ወቀት፣ በፍቺ፣ መለያየት፣ የሚወዱት ሰው መሞት፣ አዲስ ፍቅረኛ፣ ልጆች አድገው ቤት ሲለቁ፣ 30 ወይም 40 ዓመት ሲሞላ፣ ወዘተ...

እንግዲህ ይህን ቀውስ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ጉዳይ አለ። አንድ ግለሰብ የራሱ ህይወት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ለራሱ እያወቀ ነገር ግን አጠቃላይ የሰወች ኑሮ ትርጉም የለሽና አላማም የሌለው መሆኑን ሲገነዘብ በጭንቅላት ውስጥ ፍትጊያ (cognitive dissonance ) ይፈጥራል። ይህ ፍትጊያ የከባቢው ባህልና እራሱ አይምሮአችን በደመነፈስ እኒህን ለመከላከል የፈጠራቸውን የመከላከያ መሳሪያወች ያሸንፋል። ስለዚህ የኅልውና ቀውስ በሁሉም ሰው በሁሉም ህብረተሰብ ኅልው በመሆን ብቻ የሚፈጠር መሰረታዊ ጥያቄ ነው። የኅልውነት ፍልስፍና እንግዲህ የሚለው፣ እያንዳንዱ ግለሰብ የየራሱን ህይወት ትርጉምና አላማ በማስቀመጥ ይህን ቀውስ በበቂ ሁኔታ መፍታት ይችላል።