የተፈጥሮ ቁጥር
(ከየተፈጥሮ ቁጥር (ናቹራል ነምበር) የተዛወረ)
በሂሳባዊ አጠቃቀም የተፈጥሮ ቁጥር የሚባሉት ነገሮችን ለመቁጠር (8 ተማሪዎች አሉ።) እና ደረጃን ለመግለጽ ( ወደ አዲስ አበባ ስመጣ 4ኛ ግዜዬ ነው።) የመንጠቀመባቸው ቁጥሮች ናቸው።
አልጀብራዊ ባህሪዎች
ለማስተካከልድምር (+) እና ብዜት (×) በመጠቀም በተፈጥሮ ቁጥሮች ላይ የተወሰኑ ጸባዮችን ማየት ይቻላል።
- በድምር እና ብዜት ዝግ፡ ለማንኛውም ሁለት የተፈጥሮ ቁጥሮች መ እና ቀ ካሉን፣ መ+ቀ እና መ×ቀ ሌላ የተፈጥሮ ቁጥር ይሰጣሉ
- የልዩ አባል መኖር፡ ለማንኛውም የተፈጥሮ ቁጥር መ፣ መ+0=መ እና መ×1=መ
- በዜሮ አለመካፈል፡ ለማንኛውም ሁለት የተፈጥሮ ቁጥሮች መ እና ቀ ካሉን፣ መ×ቀ=0 ከሆነ መ=0 ወይም ቀ=0