የብርሃን ፍጥነት
የፀሐይ ብርሃን መሬት ለመድረስ 8 ደቂቃ ከ19 ሰኮንድ ይወስዳል |
ትክክልኛ ዋጋ = 299,792,458 ሜትር በሰኮንድ |
ተቀራራቢ ዋጋ = 300,000 ኪሎሜትር በሰኮንድ |
የብርሃን ፍጥነት በ c ምልከት ሲወከል፣ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ከፍተኛ አስተዋጾ ያለው የተፈጥሮ ቋሚ ቁጥር ነው። ብርሃን በቅጽበት ሳይሆን በተወሰነ ፍጥነት እንደሚጓዝ ቀደምት ሳይንቲስቶች የደረሱበት ጉዳይ ነው። የብርሃን ፍጥነት ለብርሃን ብቻ ሳይሆን ለብርሃን ቤተሰብ ለሆኑት ለኮረንቲና ማግኔት ማዕብሎች ያገለግላል። በአሁኑ ዘመን እንደተለካ፣ የብራሃን ፍጥነት በጥልቁ 299,792,458 ሜትር በሰኮንድ[1] ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የብርሃን ጨረር ከፀሐይ ተነስቶ መሬት ለመድረስ 8 ደቂቃ ይፈጅበታል ወይም ደግሞ አንድ የብርሃን ጨረር በየአንድ አንዷ ሰከንድ ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ሜትር (300 ሺህ ኪሎ ሜትር) ይጓዛል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ Penrose, R (2004). The Road to Reality: A Complete Guide to the Laws of the Universe. Vintage Books. pp. 410–1. ISBN 9780679776314. "... the most accurate standard for the metre is conveniently defined so that there are exactly 299,792,458 of them to the distance travelled by light in a standard second, giving a value for the metre that very accurately matches the now inadequately precise standard metre rule in Paris."