የቤት እቃ አቀማመጥ

፩. የክፍልወ ዋና አትኩረት ከሆነው (ለምሳሌ እሳት ማንደጃ፣ ወይም ቴሌቪዥን ወይም መስኮት) ፊት ለፊት ትልቁን መቀመጫ (ብዙ ጊዜ ሶፋ) በሳሎንወ ወይም ትልቁን መመገቢያ ጠረጴዛ በመመገቢያ ክፍልወ ወይም ደግሞ መኝታወን ከመኝታወ ክፍልው ያስቀምጡ።

፪. ቀጥሎ ሌሎች መቀመጫወችን (ብዙ ጊዜ ወምበሮች ወይም ደግሞ ላቭ ሲት) በ900 ከትልቁ እቃወ አጠገብ ያስቀምጡ።

፫. እኒህ እቃወች ከሚሰሩት “L” ቅርጽ በአግድም ትይዩ ሌሎች ታናና ሁለት መቀመጫወች ያድርጉ።

፬. መቀመጫወች በንዲህ መልኩ ከተረጋጉ በኋላ ከትልቁ እቃ (መቀመጫ) ጀምሮ ያለውን ክፍተት መሙላት ይጀምሩ።

፭. ቀጥሎ አንስተኛ የሆኑ የቤት እቃወችን፣ ለምሳሌ ታናናሽ ጠረጴዛወችን፣ ሶፋ ጠረጴዛወችን፣ ምንጣፎችን ከመቀመጫወቹ አንጻር ይደርድሩ።

፮. በችግን ማፍያ ውስጥ የተቀመጡ ትንንሽ አትክልቶችን ከቤት እቃወ መካከል ያስቀምጡ። በባዶ ቦታ በሩቁ ለብቻቸው አያስቀምጡ።

፯. የትራስጌ መብራቶች፣ የወለል መብራቶችን ያስቀምጡ። መብራቶቾን በ3ነጥብ (3ማዕዘን ቅርጽ) ለማስቀመጥ ይሞክሩ።

፰. በርወንና መተላለፊያወን በቤት እቃወት እንዳልተዘጉ ያረጋግጡ። በቤትወ ውስጥ ሰወች እንደልባቸው መተላለፍ ይችላሉ? ወሬስ በመካከል በሚተላለፍ ሰው ሳይቋረጡ እንግዶች ማውራት ይችላሉ? የቤትወ መብራቶች 3 ማዕዘን ቅርጽ ይሰጣሉ?


የሳሎን ቤት ዕቃ አደራደር
የመኝታ ቤት ዕቃ አደራደር መምሪያ