የበረሃዋ ድመት
የምትገኝበት አካባቢ
ለማስተካከልክብደት
ለማስተካከልተባዕቱ ከ2 እስከ 3 ኪሎ ግራም
ርዝመት (ጅራትን አይጨምርም)
ለማስተካከልከ40 እስከ 57 ሴንቲ ሜትር
ጅራት
ለማስተካከልከ20 እስከ 30 ሴንቲ ሜትር
ባሕርይ
ለማስተካከልጆሯቸው ከሩቅ ስለሚሰማ የሚያድኑት እንስሳ ከመሬት በታች ቢሆንም እንኳ ሊያገኙት ይችላሉ። ተባዕቱ ድመት ተጓዳኝ ለማግኘት ቀጭን የሆነ ኃይለኛ ጩኸት ያሰማል። እንስቷም ይህንን ድምፅ ከረጅም ርቀት መስማት ትችላለች። መዳፎቻቸው በፀጉር የተሸፈኑ ናቸው፤ ይህም በሚሄዱበት ጊዜ አሸዋ ውስጥ እንዳይሰምጡ የሚረዳቸው ከመሆኑም ሌላ መዳፋቸውን ቅዝቃዜም ሆነ ሙቀት እንዳይጎዳው ይከላከልላቸዋል። የጆሮዎቻቸው ውስጠኛ ክፍል ጥቅጥቅ ባለ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ መሆኑ ነፋስ በሚኖርበት ጊዜ አሸዋ ጆሯቸው ውስጥ እንዳይገባ ይከላከልላቸዋል። የእነዚህ ድመቶች መዳፍ ጥቅጥቅ ባለ ፀጉር የተሸፈነ በመሆኑ ዱካቸውን ተከታትሎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። እነዚህ ድመቶች ከሚበሉት እንስሳ በሚያገኙት ውኃ ብቻ መኖር ይችላሉ። የካራኩም በረሃ አሸዋ እስከ 80 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ሙቀት ሊኖረው ይችላል። በሌሎች ጊዜያት ደግሞ የሙቀቱ መጠን ከዜሮ በታች እስከ 25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊወርድ ይችላል።