የቀድሞና የወደፊቱ ንጉሥ
የቀድሞና የወደፊቱ ንጉሥ (እንግሊዝኛ፦ The Once and Future King) በእንግሊዛዊው ደራሲ ቴረንስ ዋይት በ1950 ዓ.ም. የታተመ ልብ ወለድ መጽሐፍ ነው። (መጀመርያው ክፍል «በአለቱ ውስጥ ሰይፉ» በ1930 ዓ.ም. ታተመ።)
ልብ ወለዱ ስለ አፈ ታሪካዊው የብሪቶናውያን ንጉስ አርሰር ነው። አርሰር በውነት ታሪካዊ ንጉሥ እንደ ሆነ እጅግ አጠያያቂ ቢሆንም፣ በዘመናት ላይ አያሌው ትውፊቶችና አፈታሪኮች ስለርሱ ተበዙ። (ዕውነተኛ ሰው ከሆነ ንጉሥ ሳይሆን ምናልባት በ500 ዓም ግድም በተፈጸመው በባዶን ውግያ የብሪቶኖች አለቃ ሊሆን ይቻላል።) በአንዱ ትውፊት ዘንድ ንጉሥ አርሰር በሮማይስጥ «Rex quondam rex denique» (የቀድሞና የወደፊት ንጉሥ) የሚል ጥቅስ የተጻፈለት በመሆኑ፣ የዚህ መጽሐፍ አርዕስት ከዚያ ተወሰደ። ይኸኛው መጽሐፍ ደራሲ ግን የአርሰር ታሪክ ሆን ብሎ ከሌሎች ዘመኖች ጋር እያቀላቀለ ስለ ቀኑም ፖለቲካ (በተለይም ስለ 2ኛው አለማዊ ጦርነት) ብዙ ትችቶች በማሳኩ አስቂኝና አዝናኝ ዝነኛ ጽሑፍ አቅርቧል።
- ድርሰቱ በሙሉ (እንግሊዝኛ)