የቀን መቁጠሪያ
የቀን መቁጠሪያ ወይም ካሌንዳር ማለት አንድ ድርጊት የተፈጸመበት ቀን፣ ወር ወይም አመት ወዘተ. በቅደም-ተከተል ለማወቅ የሚጠቀም ዘዴ ነው። እንዱሁም ወደፊት ለሚሆኑ ድርጊቶች ለመዘጋጀት ወይም ለማቀድ የሚጠቀም መሣርያ ነው።
በታሪክ ላይ እንደ ባሕሎቹ ልዩነት ብዙ ልዩ ልዩ ዘዴዎችና ለውጦች ተፈጽመዋል። የዓመትና የወሮች አከፋፈል ባጠቃላይ በፀሐይ ወይንም በጨረቃ ረገዶች በጠፈር ውስጥ ከመሬት ላይ ሲታዩ በሚሉ አከፋፈሎች ነው። ፀሐይም በመሃሉ ቢታይ፣ መሬት በየወሩ 1/12ኛ ያሕል ምኋር ይጓዛል። በሰዓት መልክ ላይ እንደ መሠለ፣ ከ#1 እስከ #12 ክፍሎች በመሃሉ ዙሪያ ተካፍለዋል፤ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ምድሪቱ አንድ መላ ክብ ምኋር ታደርጋለች። ክረምትና በጋ፣ ሌሎችም ወራቶች ሁልጊዜ በአመቱ ውስጥ በተጠበቀው ጊዜ እንዲመጡ ያገለገለ መለኪያ ነው።
የቀን፣ የሳምንትና የወር አከፋፈል ይሁንና የዓመታት አቆጣጠር ደግሞ በየባሕሉ ወይም በየዘዴው ይለያያል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2010 ዓመተ ምኅረት ሲሆን፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ይህ በከፊል 2017 እ.ኤ.አ. እና 2018 እ.ኤ.አ. ነው።
እስከ አሁን ድረስ በአለም ውስጥ በርካታ የጊዜ መቁጠሪያዎች ይገኛሉ፣ ለምሳለ፦