የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) የተለያዩ ማሽኖች ከሰው ተፈጥሮአዊ ክህሎቶች ጋር የሚመሳሉ ተግባሮችን የማድረግ አቅም ማለት ሲሆን እነዚህም ራስን በራስ ማስተማር እና ችግሮችን መፍታት ያካትታል። በአሁኑ ጊዜ እንደ ጎግል ያሉ የመጠይቅ ገጾች ፣ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያሽከረክሩ መኪናዎች ፣ ቁንቁን ለመተርጎም ፣ ፌስቦክ ላይ የምናውቃቸውን ሰዎች ለማገናኘት፣ ዩትዩብ ላይ ያየነውን ቪዲዮ ጋር ተያያዥነት ያለውን ምስል ለመጠቆም፣ ልዩ ልዩ በሽታዎችን ለመመርመር ወ.ዘ.ተ ጥቅም ላይ ይውላል።

አጀማመር ለማስተካከል

ለሰው ሰራሽ አስተውሎት መጀመር አለን ቱሪንግ የተባለ የሂሳብ ባለሙያ 0 እና 1ን በማቀያየር የኮምፒውተሮችን አቅም ማሳደግ እንደሚቻል ጥናት ካደረገ በኋላ ሲሆን ቱሪንግ ሰዎች እና ኮምፒውተሮች ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲያደርጉ በማድረግ እና ሌላ ገምጋሚ የተለየ ክፍል ላይ በማስቀመጥ የሰው እና የኮምፒውተሩ የትኛው እንደሆነ መለየት እንዲችሉ ፈተና አዘጋጅቶ ነበር። ይህም የቱሪንግ ፈተና (Turing Test) በመባል ይታወቃል። ገምጋሚው የትኛው መልስ የኮምፒውተሩ እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ ካልቻለ ኮምፒውተሩ ከሰዎች አስተውሎት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ችሎታ አለው ማለት ነው።

አለን ቱሪንግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አባት ተደርጎ ይቆጠራል።