የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፱

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፱

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፻፷፪ ፤ እንግዲህ እንደ ማርያም አርምሞንና ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ ማርያምስ የማይቀሙዋትን በጎ ዕድልን መረጠች ብሎ ጌታችን አመስግኑዋታልና ።
፻፷፫ ፤ አሁንም ጸጋን የሰጠ አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምነው ጸልዩ ።
፻፷፬ ፤ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ ።
፻፷፭ ፤ ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካአንቺ የተወለደውን መውለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ ።
፻፷፮ ፤ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ ።
፻፷፯ ፤ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ ።
፻፷፰ ፤ ድንግል ሆይ ረኃብና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ ።
፻፷፱ ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ ።
፻፸ ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጣን አሳስቢ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ ።
፻፸፩ ፤ አሁንም አብና ወልድን መንፈስቅዱስንም እናመስግነው ለዘላለሙ አሜን ።
፻፸፪ ፤ አንብሮ እድ ለእናቱ ስለሰጣት ጸጋ ሁሉ በዚች ቅዳሴ ላይ ስላሰለጠናት እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ። እኛንም በቸርነቱ እንናገር ዘንድ የተዘጋጀን አደረገን ምስጋና ያለው እርሱ ነው ። ጥበበኛም ነው ለዘላለሙ አሜን ።
፻፸፫ ፤ በውስጧ ይህን ቅዳሴ የሚቀድስ ካህን ድንግል ማርያምን የሚቀድስ አይደለም የሚል አገኘሁ እርሱ ይቀደሳል እንጂ የሰሙትም ሁሉ ይከብራሉ ቅድስት ድንግል ማርያም ግን በሰማይም በምድርም ዘውትር የተመሰገነች ናት ።
፻፸፬ ፤ የሚቀበለው የልመናዋ ክብር ፍፁም የሆነ የረድኤትዋ ሀብት ጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚመላ የተወደደ የልጅዋ ቸርነት ከሁላችን ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን ።