የሐዋርያት ሥራ ፪
የሐዋርያት ሥራ
1፤በዓለ፡ኀምሳ፡የተባለውም፡ቀን፡በደረሰ፡ጊዜ፥ዅሉም፡ባንድ፡ልብ፡ኾነው፡ዐብረው፡ሳሉ፥
2፤ድንገት፡እንደሚነጥቅ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ከሰማይ፡ድምፅ፡መጣ፥ተቀምጠው፡የነበሩበትንም፡ቤት፡ዅሉ፡
3፤እንደ፡እሳትም፡የተከፋፈሉ፡ልሳኖች፡ታይዋቸው፤በያንዳንዳቸውም፡ላይ፡ተቀመጡባቸው።
4፤በዅሉም፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሞላባቸው፥መንፈስም፡ይናገሩ፡ዘንድ፡እንደ፡ሰጣቸው፡በሌላ፡ልሳኖች፡ይናገሩ፡
5፤ከሰማይም፡በታች፡ካሉ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡በጸሎት፡የተጉ፡አይሁድ፡በኢየሩሳሌም፡ይኖሩ፡ነበር፤
6፤ይህም፡ድምፅ፡በኾነ፡ጊዜ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ተሰበሰቡ፥እያንዳንዱም፡በገዛ፡ቋንቋው፡ሲናገሩ፡ይሰማ፡ስለ፡
7፤ተገርመውም፡ተደንቀውም፡እንዲህ፡አሉ፦እንሆ፥እነዚህ፡የሚናገሩት፡ዅሉ፡የገሊላ፡ሰዎች፡አይደሉምን፧
8፤እኛም፡እያንዳንዳችን፡የተወለድንበትን፡የገዛ፡ቋንቋችንን፡እንዴት፡እንሰማለን፧
9፤የጳርቴና፡የሜድ፡የኢላሜጤም፡ሰዎች፥በኹለት፡ወንዝም፡መካከል፡በይሁዳም፡በቀጰዶቅያም፡በጳንጦስም፡
10፤በፍርግያም፡በጵንፍልያም፡በግብጽም፡በቀሬናም፡በኩል፡ባሉት፡በሊብያ፡ወረዳዎች፡የምንኖር፥በሮሜም፡
11፤የቀርጤስና፡የዐረብ፡ሰዎች፥የእግዚአብሔርን፡ታላቅ፡ሥራ፡በልሳኖቻችን፡ሲናገሩ፡እንሰማቸዋለን።
12፤ዅሉም፡ተገረሙና፡አመንትተው፡ርስ፡በርሳቸው፦እንጃ፥ይህ፡ምን፡ይኾን፧አሉ።
13፤ሌላዎች፡ግን፡እያፌዙባቸው፦ጕሽ፡የወይን፡ጠጅ፡ጠግበዋል፡አሉ።
14፤ነገር፡ግን፥ጴጥሮስ፡ከዐሥራ፡አንዱ፡ጋራ፡ቆመ፥ድምፁንም፡ከፍ፡አድርጎ፡እንዲህ፡ሲል፡
ተናገራቸው፦አይሁድ፡በኢየሩሳሌምም፡የምትኖሩ፡ዅላችኹ፥ይህ፡በእናንተ፡ዘንድ፡የታወቀ፡
15፤ለእናንተ፡እንደ፡መሰላችኹ፡እነዚህ፡የሰከሩ፡አይደሉም፥ከቀኑ፡ሦስተኛ፡ሰዓት፡ነውና፤
16፤ነገር፡ግን፥ይህ፡በነቢዩ፡በኢዮኤል፡የተባለው፡ነው።
17፤እግዚአብሔር፡ይላል፦በመጨረሻው፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ሥጋ፡በለበሰ፡ዅሉ፡ላይ፡ከመንፈሴ፡
ያያሉ፥ሽማግሌዎቻችኹም፡ሕልም፡ያልማሉ፤
18፤ደግሞም፡በዚያች፡ወራት፡በወንዶችና፡በሴቶች፡ባሪያዎቼ፡ላይ፡ከመንፈሴ፡አፈሳለኹ፡ትንቢትም፡
19፤ድንቆችን፡በላይ፡በሰማይ፥ምልክቶችንም፡በታች፡በምድር፡እሰጣለኹ፤ደምም፡እሳትም፡የጢስ፡ጭጋግም፡
20፤ታላቅ፡የኾነ፡የተሰማም፡የጌታ፡ቀን፡ሳይመጣ፡ፀሓይ፡ወደ፡ጨለማ፡ጨረቃም፡ወደ፡ደም፡ይለወጣሉ።
21፤የጌታን፡ስም፡የሚጠራም፡ዅሉ፡ይድናል።
22፤የእስራኤል፡ሰዎች፡ሆይ፥ይህን፡ቃል፡ስሙ፤ራሳችኹ፡እንደምታውቁ፥የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡እግዚአብሔር፡
በመካከላችኹ፡በርሱ፡በኩል፡ባደረገው፡ተኣምራትና፡በድንቆች፡በምልክቶችም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ለእናንተ፡
23፤ርሱንም፡በእግዚአብሔር፡በተወሰነው፡ዐሳቡና፡በቀደመው፡ዕውቀቱ፡ተሰጥቶ፡በዐመፀኛዎች፡እጅ፡
24፤እግዚአብሔር፡ግን፡የሞትን፡ጣር፡አጥፍቶ፡አስነሣው፥ሞት፡ይይዘው፡ዘንድ፡አልቻለምና።
25፤ዳዊት፡ስለ፡ርሱ፡እንዲህ፡ይላልና፦ጌታን፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡አየኹት፥እንዳልታወክ፡በቀኜ፡ነውና።
26፤ስለዚህ፥ልቤን፡ደስ፡አለው፥ልሳኔም፡ሐሤት፡አደረገ፥ደግሞም፡ሥጋዬ፡በተስፋ፡ያድራል፤
27፤ነፍሴን፡በሲኦል፡አትተዋትምና፥ቅዱስኽንም፡መበስበስን፡ያይ፡ዘንድ፡አትሰጠውም።
28፤የሕይወትን፡መንገድ፡አስታወቅኸኝ፤ከፊትኽ፡ጋራ፡ደስታን፡ትሞላብኛለኽ።
29፤ወንድሞች፡ሆይ፥ስላባቶች፡አለቃ፡ስለ፡ዳዊት፡እንደ፡ሞተም፡እንደ፡ተቀበረም፡ለእናንተ፡በግልጥ፡
እናገር፡ዘንድ፡ፍቀዱልኝ፤መቃብሩም፡እስከ፡ዛሬ፡በእኛ፡ዘንድ፡ነው።
30፤ነቢይ፡ስለ፡ኾነ፥ከወገቡም፡ፍሬ፡በዙፋኑ፡ያስቀምጥ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡መሐላ፡እንደ፡ማለለት፡
31፤ስለክርስቶስ፡ትንሣኤ፡አስቀድሞ፡አይቶ፥ነፍሱ፡በሲኦል፡እንዳልቀረች፡ሥጋውም፡መበስበስን፡እንዳላየ፡ተናገረ።
32፤ይህን፡ኢየሱስን፡እግዚአብሔር፡አስነሣው፡ለዚህም፡ነገር፡እኛ፡ዅላችን፡ምስክሮች፡ነን፤
33፤ስለዚህ፥በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሎና፥የመንፈስ፡ቅዱስን፡የተስፋ፡ቃል፡ከአብ፡
34-35፤ዳዊት፡ወደ፡ሰማያት፡አልወጣምና፥ነገር፡ግን፥ርሱ፦ጌታ፡ጌታዬን፦ጠላቶችኽን፡የእግርኽ፡
36፤አለ፦እንግዲህ፡ይህን፡እናንተ፡የሰቀላችኹትን፡ኢየሱስን፡እግዚአብሔር፡ጌታም፡ክርስቶስም፡እንዳደረገው፡
37፤ይህንም፡በሰሙ፡ጊዜ፡ልባቸው፡ተነካ፥ጴጥሮስንና፡ሌላዎችንም፡ሐዋርያት።ወንድሞች፡ሆይ፥ምን፡
38፤ጴጥሮስም፦ንስሓ፡ግቡ፥ኀጢአታችኹም፡ይሰረይ፡ዘንድ፡እያንዳንዳችኹ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡ተጠመቁ፤የመንፈስ፡ቅዱስንም፡ስጦታ፡ትቀበላላችኹ።
39፤የተስፋው፡ቃል፡ለእናንተና፡ለልጆቻችኹ፡ጌታ፡አምላካችንም፡ወደ፡ርሱ፡ለሚጠራቸው፡በሩቅ፡ላሉ፡
40፤በብዙ፡ሌላ፡ቃልም፡መሰከረና፦ከዚህ፡ጠማማ፡ትውልድ፡ዳኑ፡ብሎ፡መከራቸው።
41፤ቃሉንም፡የተቀበሉ፡ተጠመቁ፥በዚያም፡ቀን፡ሦስት፡ሺሕ፡የሚያኽል፡ነፍስ፡ተጨመሩ፤
42፤በሐዋርያትም፡ትምህርትና፡በኅብረት፡እንጀራውንም፡በመቍረስ፡በየጸሎቱም፡ይተጉ፡ነበር።
43፤ነገር፡ግን፥በሰው፡ዅሉ፡ፍርሀት፡ኾነ፤በሐዋርያትም፡እጅ፡ብዙ፡ድንቅና፡ምልክት፡ተደረገ።
44፤ያመኑትም፡ዅሉ፡ዐብረው፡ነበሩ፤
45፤ያላቸውንም፡ዅሉ፡አንድነት፡አደረጉ።መሬታቸውንና፡ጥሪታቸውንም፡እየሸጡ፥ማንኛውም፡እንደሚፈልግ፡
46፤በየቀኑም፡ባንድ፡ልብ፡ኾነው፡በመቅደስ፡እየተጉ፡በቤታቸውም፡እንጀራ፡እየቈረሱ፥በደስታና፡በጥሩ፡
47፤እግዚአብሔርንም፡እያመሰገኑ፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፡ሞገስ፡ነበራቸው።ጌታም፡የሚድኑትን፡ዕለት፡ዕለት፡በእነርሱ፡ላይ፡ይጨምር፡ነበር።