አለማየሁ እሸቴ (1941-2021) ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃል።

አለማየሁ እሸቴ

የህይወት ታሪክ

ለማስተካከል

አለማየሁ እሸቴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርበኞች ት/ቤት ተከታትሎ ባደረበት ጥልቅ የሙዚቃ ስሜትና ባለው ግሩም ተሰጥኦ ተገፋፍቶ ድምጻዊነቱን በፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል ጀመረ። ብዙዎቹ የአለማየሁ ዘፈኖች ከስሜት በሚያፈልቃቸው ዜማዎች ዘመናዊነት የሚታይባቸውና ከውጭ ሀገር ዘፈኖች ጋር ይመሳሰላሉ።[1]

የሥራዎች ዝርዝርና ውጤት

ለማስተካከል

ቀደም ሲል «እዬዬ»፣ «ማሪኝ ብዬሻለሁ» በተሰኙት ዜማዎቹና «ስቀሽ አታስቂኝ»፣ «ማን ይሆን ትልቅ ሰው»፣ «እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ» በሚላቸው ዘፈኖቹ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አርቲስት ነው። ለሚስቱና ለልጆቹ ማቆላመጫ «ውዷ ባለቤቴ!» የምትል ዜማ ተጫውቷል።[1]

አለማየሁ እስካሁን ድረስ ከ፷፪ በላይ ዜማዎቹ በሸክላ ተቀርጸው ፲፭ ሺህ ያህሉ ተሽጠውለታል።[1]

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 30-31". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.