እዚህ "ሸዋ" መጣጥፍ ላይ ሰሞኑን የሚካሄደው እንቅስቃሴ አሳሳቢ ይመስለኛል። ከ25 ፌብሩዌሪ 2011 ጀምሮ 146.82.18.239/ 125.167.79.101 / 69.31.101.56 / 195.53.203.127 (ምናልባት አንድ ሰው ሊሆን ይችላል) Translated from the English version of Wikipidia http://en.wikipedia.org/wiki/Shewa በሚል ሳይታረም፤ ሳይስተካከል፤ በትክክሉም ሳይተረጎም፤ የቀረበውን ስድ ጽሑፍ እኔም ሆንኩ Codex Sinaiticus ያስተካክልነውን በተደጋጋሚ ይገለበጣል። ይሄ የጥፋት ድርጊት ነው ወይስ የዊኪፔድያ አሠራር ያልገባው ሰው ነው? በበኩሌ በመዘንጋት ካልሆነ በተጠቃሚ ስም የማይገባ (ማለትም የኮምፑተር i.p. address ብቻ በማሳየት)አባል ዓላማው አይገባኝም። --Bulgew1 08:16, 1 ማርች 2011 (UTC)Reply

ገጹ ተቆልፏል።

ይህ በውነት ጉድ ሥራ ነው። ደግሞ የልጅነት ሥራ ይመስላል። አቅራቢው ከእንግሊዝኛው መጣጥፍ ትርጉም እንዳገኘ እርግጥኛ ነው። ሆኖም ይህን ማድረግ ከትርጉም መስሪያ ቤት በብር (ገንዘብ) ቀላል ስለ ሆነ፣ አቅራቢው እራሱ አማርኛ መቻሉ እርግጥኛ አይሆንም። ፈቃደ (ውይይት) 12:26, 1 ማርች 2011 (UTC)Reply

የኔ ጥያቄ የሸዋ ታሪክን በተመለከተ ነው። የንግሊዘኛው ዝርዝር ጥሩ ቢሆንም፡ የአማርኛው ዝርዝር በጭራሽ የተበላሸ ነው። የሸዋ ታረክ በትክክል አልተቀመጠም። ፈቃደ የሚባለው አዘጋጁ በሸዋ ላይ ጥላቻ ያለው ሰው ይመስላል። በመሆኑም እስኪተክከል ድረስ ጥረት አደርጋለሁ። አቶ ፈቃደ ፡ የሸዋን ታሪክ በማበላሸት አሁን ተሳክቶልሃል፡ ነገር ግን መስተካከሉ አይቀርም።

ይህ መስቃ ነው ሸዋን በ1985 ዓ.ም. ነበርኩ በጣም ቆንጆ ነበር አዲስ አበባ፣ ሻሸመኔ፣ ዝዋይን አይቼያለሁ። ለምን አልወደድኩም ትለኛለህ እኔ በነፍስ ወጃታለሁ! በገጹ ለይ ተጻፈው ታሪክ እንዴት ትክክል አይደለም? አሁን በHgetnet በመቆለፉ ለግዜው እርማት በዚህ ገጽ ላይ መጠይቅ ይቻላል። ፈቃደ (ውይይት) 04:05, 2 ኤይፕርል 2011 (UTC)
በገጹ ላይ የተጻፈው ታሪክ ልክ ካልሆነ ከነማስረጃው እንዲያቀርብ፣ ዋቢ መጽሃፍትን እንዲያጣቅስ እመክረዋለሁ። Bulgew1 ስለ ሸዋ ባለው የበለጠ ዕውቀት ነገሩን መርምረን ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከባድ አይሆንም። ያለምንም ማስረጃ እንዲሁ አንተን መወንጀል ግን ከውክፒዲያ ፖሊሲ ጋር ስለሚጋጭ ጽሑፉ እንዲከፈት የሚያበረታታ ተግባር አይደለም።
አሁን ለDagne888 እምመክረው፣ ዋቢ መጽሐፍትን ጠቅሶ ሊያቀርብ ያሰባቸውን ጽሑፎች እዚህ ላይ ይጻፍና፣ Bulgew1 ታማኝነታቸውን ካረጋገጠ በኋላ ጽሑፉ ይከፈታል። Hgetnet 19:12, 2 ኤይፕርል 2011 (UTC)
ሰላም Hgetnetፈቃደ ፦ Dagne888 ይሁን አይሁን ለማወቅ ቢያስቸግረኝም፤ 'መርዝ' በሚል የብዕር ስም የሚጽፍ/የምትጽፍ ዋርካ ላይም ስት/ሲውነጅለን ሰንብታለች/ሰንብትዋል። "ተርጓሚ ተብየዎቹ እንዴት እንደተረጎሙት ተመልከቱና ፍረዱ። ማነው እነዚህን እንግሊዘኛ የማይችሉትን ለዊኪፒዲያ የቀጠራቸው ? ምናልባትም ለተንኮል ይሆናል እንደዚህ አዛብተው የተረጎሙት " "ዊኪፒዲያ ውስጥ የሸዋን ታሪክ አታበላሹ" በሚል ገጽ ላይ ደግሞ ይሄው መርዝ "ሸዋ እስከ 1889 ድረስ የኢትዮጵያ ግዛት አለመሆኗን የማያውቅ ካለ መጽሀፎችን ማገላበጥ አለበት ይህንን ታሪክ ለመደበቅ አጋሜዎች በጣም እየጣሩ ነው እኔ ዊኪፒዲያ ላይ ሳስተካክል ሌላው መጥቶ ያበላሸዋል ተመልከቱት " ብሎ አስቀምጧል። በእኔ ግምት ከዚህ በፊት ስለሸዋ የተጻፈውን በመመላለስ፣ ያለአንዳችም (ከእንግሊዝኛው ዊኪፔዲያ በስተቀር)መረጃ፤ ሲ/ስትገለባብጥ የነበረው/ችው ሰው እና 'መርዝ'ም Dagne888 አንድ ሰው ናቸው። አንዳንድ ሰዎች (መነሻ ዓላማቸው ምንም ሆነ ምን) የፈለጉትን (የተንኮልም ይሁን የአለማውቅ) ካልሆነላቸው በስተቀር የሰውን ህልውና ለመዝለፍ እና ለመሳደብ ወደኋላ የማይሉ (በመረጃ፤ በትህትና በቀረበ እውነት-አዘል ሙግት፤ በበሰለ አመለካከት፤ ወዘተ) የማስተናገድ ችሎታም ሆነ አስተዳደግ ስለሌላቸው፤ የኢትዮያን ባህልም ሆነ ታሪክ ለትውልድ በሐቅ ከማሳወቅ ይልቅ የዘር ፖለቲካን ማራመድ ብቻ የሚፈልጉ ሆነው እናገኛቸዋለን ። የአማርኛ ዊኪፔዲያ የፖለቲካ መድረክ አይደለም! ወይም የሰውን የዘር አመጣጥ መጠየቂያ/መተቻ ቦታ አይደለም። ይህ በንዲህ እንዳለ ጌትነት Dagne888 በዋቢ ምንጮች የተደገፈ ጽሑፉን ያቅርብ ያልከው ትክክለኛ ነውና እስቲ መረጃዎቹ በዚህ በሸዋ ርዕስ የቀረበውን የሚያስተባብሉ መረጃዎች እንደሆኑ እንያቸው።--Bulgew1 20:46, 2 ኤይፕርል 2011 (UTC)
ሰላም፣ እኔ ምለው ይህ መጣጥፍ ዋቢ ምንጮች ቢኖሩት ጥሩ ነው። ከውክፔዲያ ዋና መመሪያዎች ውስጥ አንዱ ዕውቅና ያላቸው ዋቢ መጻሕፍትና ድረ ገጾችን መጥቀስ ነው። Elfalem 02:47, 3 ኤይፕርል 2011 (UTC)

በመጀመሪያ ደረጃ የሚያናድደው ነገር ፣ የሸዋን ታሪክ እኛ ሸዌዎቹ ማስቀመጥ ሲገባን የሸዋ ደም የሌለው ሰው ስለኛ ታሪክ መከራከሩ ያናድዳል የእንግሊዘኛው ጽሁፍ እንዲሁ አልተጻፈም። ዋቢ ከስሩ ተጽፏል። ለምን አታዩትም? ^ G.W.B. Huntingford, The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, (Oxford University Press: 1989), p. 76 ^ Mordechai Abir, Ethiopia: the Era of the Princes (London: Longmans, 1968), pp. 144ff. የተክለ ጻዲቅ መኩሪያን ( ከይኩነ አምላክ እስከ ቴዎድሮስ) መጽሃፍ ተመልከቱት። የኢትዮጵያ ታሪክና የሸዋ ታሪክ ለብቻው ተጽፏል። ቴዎድሮስ ሸዋን የወረረው፣ ሸዋን ከኢትዮፕጵያ ጋር ለመደባለቅ አይደለም እንዴ? ለማንኛውም ለሁሉም ቀን አለው፣ አሁን እናንተ ታሪኩን ብታበላሹት የሚስተካከልበት ቀን ይመጣል።

ለተፈጠረው ስህተት ከነአረፍተ ነገሩ እየጠቀስክ ጻፍ። ማስተካከያውን ደግሞ ከዋቢ መጻህፍት እያጣቀስክ አሳይ። የወል ክስ ለማረጋገጥ ያስቸግራል። ስለሆንም ለማስተካከልም እማይቻል ነው። Hgetnet 23:19, 3 ኤይፕርል 2011 (UTC)

እኔም ሆንኩ ወዳጆቼ ለዊኪፒዲያ ባለቤቶች በተደጋጋሚ ኮምፕሌን ማድረግ እንጀምራለን ብዛት ያለው ሰው ሲናገር አንድ ነገር ያደርጋሉ ጥሩነቱ ዊኪፕዲያ ያንተ አለመሆኑ ነው

መልካም ዕድል Hgetnet 00:00, 4 ኤይፕርል 2011 (UTC)
የከበረ ሰላምታ ለሁላችሁም። እኔ የዚህ ሰው ቅሬታና ሙግት ምንም ሊገባኝ አልቻለም። ሸዋ ራሱን የቻለ ግዛት ነበር አላላችሁም እንደሆነ የሚለው፤ የዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ አረፍተ ነገር “ሽዋ በኢትዮጵያ ገጸ ምድር መሃል ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሥፍራ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት በሉዐላዊነት በራሱ መሪዎች ሲተዳደር የኖረ የኢትዮጵያ አካል ሲሆን፣…” ስለሚል ይሄ የቅሬታው ምክንያት ሊሆን አይችልም።

በእንግሊዝኛው የተጻፈውን በትክክል አልተረጎማችሁም እንደሆነ የሚባለው፦ በእንግሊዥኛው በዋቢነት የተጠቀሱት ሁለቱ ምንጮች የተያያዙት ፦ (1) Shewa first appears in the historical record as a Muslim state, which G.W.B. Huntingford believed was founded in 896, and had its capital at Walalah.[1] This state was absorbed by the Sultanate of Ifat around 1285. Recently, three urban centers thought to be part of the Islamic kingdom of Shewa was discovered by a group of French archaeologists. ሲሆን በአማርኛው ጽሑፍ “ሸዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ የተመዘገበችው በ896 እ.ኤ.አ. በተመሠረተውና ዋና ከተማውን ወለላ (Walalah)ላይ አድርጎ በነበረው የእስላም ግዛት ውስጥ ነው በማለት በኢትዮጵያ ታሪክ ዘጋቢዎች ይታመናል። ከነዚህም አንድ፣ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ትምህርታዊ መጽሐፍትን የደረሰው ሀንቲንግፎርድ (G.B.W. Huntingford) ነው። ይህ ግዛት ወደ ፲፪፻፸፮ ዓ/ም በይፋቱ ሱልጣን ሥር ተጠቃለለ። በቅርብ ጊዜ በፈረንሳይ የሥነ-ቅርስ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ሦስት ቦታዎች የሸዋ እስላማዊ ንጉዛት(በዘውድ የሚተዳደር ግዛት) የከተማ ማእከላት ናቸው ተብለው ተገምተዋል።” ተብሎ ተተርግሟል።

(2) The Shewan ruling family was founded by Negassie in the late 17th century, who consolidated his control around Yifat. Traditions recorded about his ancestry vary: one tradition, recorded in 1840, claims his mother was the daughter of Ras Faris, a follower of Emperor Susenyos who had escaped into Menz; another tradition told by Serta Wold, a councilor of Sahle Selassie, was that Negassie was a male-line descendant of Yaqob, the youngest son of Lebna Dengel, and thus assert descent from the ancient ruling Solomonic dynasty.[2] Thus the ruling family of Shewa were considered the junior branch of the Solomonic dynasty after the senior Gondar branch.

“የሸዋ መሪዎች ቤተሰብ የተጀመረው በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነጋሲ ክርስቶስ ነው። ነጋሲ ይፋት አካባቢ ያለውን ቦታ ይቆጣጠር ጀመር። በይፋዊ ታሪክ፣ የነጋሢ አባት ልስበ ቃል (በመንዝ የአጋንቻ ጌታ) በአጼ ልብነ ድንግል ታናሽ ልጅ በያዕቆብ በኩል የሚመጣ በአባት በኩል የዘር ሐረግ ያለው ነው ይላል። ይህም ማለት ከሰለሞን ስርወ መንግስት ጋር የተያያዘ ነው ማለት ነው። በዚህ መሰረት የሸዋ ነገስታት የሰለሞን ስርወ መንግስት አነስተኛው ቅርንጫፍ ሲሆኑ የጎንደሩ ደግሞ ትልቁ የሰለሞን ስርወ መንግስት ቅርንጫፍ ነው ማለት ነው። ሆኖም ስለ ነጋሲ የዘር አመጣጥ ሌሎችም አባባሎች አሉ።” ተብሎ ተተርጉሟል።

እንግዲህ በዚህ የአማርኛ ጽሑፍ ላይ በ”ቀደምት ታሪክ” አርዕስት ሥር፤ ከሸዋ መሳፍንት ማዕረግ በስተቀር ይሄው ነው። ታዲያ ይሄን ሰውዬ እስከዚህ የሚያሟግተውና የስድ፣ የባለጌ ዘለፋ ውስጥ የሚያስኬደው ምንድን ነው? በጣም ይገርማል!--Bulgew1 01:31, 4 ኤይፕርል 2011 (UTC)

ከላይ ከተጻፈው ውስጥ ስህተት የለም። Hgetnet 02:36, 4 ኤይፕርል 2011 (UTC)
Return to "ሸዋ" page.