ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 3
ጥቅምት ፫
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የክብር ዘበኛ ሠራዊት ሸንጎ ሊቀ መንበር በደርግ ተያዙ። በዚሁ ዕለት የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ፩መቶ ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት ለቀድሞ ባለ-ሥሎጣኖቻቸው ሰጥተዋል ተባለ።
- ፲፱፻፸፬ዓ/ም - የምስር ምክትል ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ የቀድሞው ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት በተገደሉ በሳምንቱ የአገሪቱን ፕሬዚደንታዊ ሥልጣን ተረከቡ።
- ፲፱፻፹፯ ዓ/ም - የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሓቅ ራቢን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስምዖን ፔሬዝ የዓመቱን የኖቤል ሰላም ሽልማት በኅብረት ተቀበሉ።