ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥር 17
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - አንደኛው የዓለም ጦርነት ከተገባደደ በኋላ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (The League of Nations) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የቀድሞው የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ በሲንጋፖር ላይ በሚካሄደው የጋራ ሀብት አገሮች ጉባዔ ላይ እንዳሉ በጄኔራል ኢዲ አሚን በተመራ ወታደራው መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።
- ፳፻፪ ዓ/ም - ከቤይሩት ከተማ ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ወአዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ፯፻፴፯ አየር ዠበብ፣ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ባልታወቀ ምክንያት ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ተፈጅተዋል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።