ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 22
- ፲፱፻፶፰ - ዓ/ም የቀድሞው የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤባሪስቴ ኪምባ እና ሌሎችም የፖለቲካ ሰዎች በአምባገነኑ ፕሬዚደንት ዮሴፍ ሞቡቱ ትዕዛዝ በሕዝብ ፊት በሞት ተቀጡ።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የናይጄሪያ ምሥራቃዊ ክፍል ቢያፍራ መገንጠሏን ስታውጅ በሁለቱ መካከል ለተለኮሰው የእርስ በእርስ ጦርነት መነሻ ምክንያት ሆነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ቆስቋሽነት የተሠየመው የሙስና እና የሥልጣን በደል መርማሪ ሸንጎ ሥራውን የሚመራበት ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።