ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 18
- ፲፯፻፲፫ ዓ/ም - ከወህኒ በወረዱ በሁለተኛው ቀን የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ልጅ አፄ በካፋ ጎንደር ላይ በጳጳሱ አባ ክርስቶዶሉ እና እጨጌ ተክለ ሃይማኖት ተቀብተው ነገሡ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - ለብሪታኒያዊው ሥራ-ፈጣሪ ዊሊያም ኖክስ ዳርሲ የሚሠሩ መሐንዲሶች ‘ማስጂዲ ሱሌይማን’ በተባለ በአሁኗ ኢራን የሚገኝ ስፍራ ላይ በመካከለኛው ምሥራቅ የመጀመሪያውን ትልቅ የነዳጅ ክምችት አገኙ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የኢንዱስትሪ እና የቴክኒክ ምርቶች አውደ ርዕይ አዲስ አበባ ላይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አሥረኛው የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ተከፈተ።