ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 1
- ፲፰፻፵፬ ዓ/ም - ራስ መኮንን ከ ልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ እና ከደጃዝማች ወልደሚካኤል ወልደ መለኮት ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ዘውዱ ወደንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ ተዛወረ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተጨፍልቀው ሕይወታቸውን አጡ።