ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 5
- ፲፱፻፲፰ ዓ.ም.፦ ቤተ ሳይዳ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ፣ አሁን የካቲት ፲፪ የተባለው) ሆስፒታል ተቋቋመ፡፡
- ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ፦ ፪ ሺህ ፻፷፰ ወታደር ያሰለፈው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት፣ ቃኘው የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የ፶ ዐለቃ ካሣ ተሰማ "እልም አለ ባቡሩ" በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - አንጋፋው የፊልም ተዋናይ ሲድኒ ፗቲዬር ‘ሊሊስ ኦፍ ዘ ፊልድ’ (Lilies of the Field) በተባለው ፊልሙ የ’ኦስካር’ ሽልማት ሲቀበል የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አ. አ.ድ) ((እንግሊዝኛ)፡ Organisation of African Unity (OAU)) የአፍሪቃ የሠራተኞች ማኅበራት የአንድነት ውል አዲስ አበባ ላይ ተፈረመ።