ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 19
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት አገራችንን ኢትዮጵያን ሲወር በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገባው ማርሻል ፒዬትሮ ባዶልዮ፤ ተሸናፊዋን አገሩን በመወከል የሽንፈቱን ስምምነት ፈረመ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ከዚያ በፊት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ በ ሶቪዬት ኅብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቾቭ ድንፋታ ተረበሸ። በዚህ ስብሰባ ላይ ክሩስቾቭ ጫማቸውን አውልቀው ጠረጴዛቸውን በመቀጥቀጥ ዓለምን አስገርመዋታል።
- ፳፻፪ ዓ/ም - በሳሞዋ ደሴቶች አጥቢያ የተከሰተው፣ በ ‘ሪክተር ሚዛን’ ስምንት ነጥብ ያስመዘገበው የመሬት እንቅጥቅጥ ‘ሱናሚ’ (tsunami) የሚባለውን የባሕር ነውጥ አስከተለ።