ዋሺንግተን ዲሲ (እንግሊዝኛ፦ Washington D.C.) የአሜሪካ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 570,898 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 38°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 77°00′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ፔንስልቬኒያ ጎዳና በ1990 ዓ.ም.

እንግሊዝ ሰዎች መጀመርያ በአካባቢው በደረሱ ወቅት (1600-1660 ዓ.ም.) በአሁኑ ዲሲ ሥፍራ ናኮችታንክ የተባለ የኗሪዎች ታላቅ መንደርና ንግድ ማዕከል ተገኘ። የአሁኑ ዋሺንግተን ከተማ የአሜሪካ አዲስ ልዩ ዋና ከተማ እንዲሆን በ1783 ዓ.ም. ተመሠረተ። በ1792 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ በይፋ ከፊላዴልፊያ ወደ ዋሺንግተን ተዛወረ።

የከተማው ስም «ዋሺንተን» የአገሩን መጀመርያውን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሺንግተንን ያከብራል። «ዲሲ» (D.C.) ማለት በእንግሊዝኛ ለ«ዲስትሪክት ኦቭ ኮሎምቢያ» (District of Columbia ወይም የኮሎምቢያ ክልል) አጭር ነው።

ደግሞ ይዩEdit

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።