ዋርካ (ድረገጽ)
ዋርካ ሳይበር ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው ድረገጽ የአማርኛ ቋንቋ የውይይት መድረክ ድረ ገጽ ነው። ይህ ድረገጽ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፊደል መወያየት ይችሉ ዘንድ በሁለት ወንድማማች ኢትዮጵያዊያን በሰኔ 1992ተፈጥሮ ዛሬ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በስፋት እያገለገለ ያለ ዌብሳይት ሆኖአል።
ይሁን እንጂ ድረገጹ እንደሚለው ከግንቦት 1998 ጀምሮ [1] Archived ጁን 21, 2007 at the Wayback Machine፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ድረገጽን ስለአገደው በአገር ውስጥ እንዳይሰራ ወይም እንዳይታይ አግዷል። ሆኖም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ብርሃኑ ሃይሉ ስዋርካ/ሳይበር ኢትዮጵያና ስለሌሎቹም ስለታገዱ ፖለቲካ ነክ ድረገጾች ጉዳይ ተጠይቀው ምንም የተከለከለ ድረገጽ የለም የማይታዩበት ምክንያትም አይታወቅም በማለት በተደጋጋሚ አስተባብለዋል። ዋርካ ወይም ሳይበር ኢትዮጵያ በምዕራቡና በዓለም ዙሪያ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊያን ሕብረተሰብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም የዕለት ከዕለት ኑሮ ስለ ፖለቲካ ወይም ስለ ባሕል እና ስነ-ጽሑፍ፣ ስነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ፍቅር፣ ሃይማኖት እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮችን ሊያወያዩ የሚችሉ በጣም ጠቃሚ መድረኮች ስላሉት መፍትሔ ያጡለትን ጉዳዮች በውይይት መፍትሔ እንደዳስገኘለት ከተጠቃሚዎች የተገኘ መረጃ ያረጋግጣል።
የውጭ መያያዣ
ለማስተካከል- ዋርካ መድረክ Archived ኖቬምበር 30, 2006 at the Wayback Machine
- ዌብሳይቶች በመንግሥት ስለመከልከላቸው (በሳይበር ኢትዮጵያ)
- ዌብሳይቶች ስለመከልከላቸው (በሌላ ምንጭ)
- ስለመከልከላቸው (በሌላ ምንጭ)
- ስለ መከልከላቸው (በሌላ ምንጭ)
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |