ወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያ
ክብር
(ከወደፊት ገስግሺ፣ውድ እናት ኢትዮጵያ የተዛወረ)
የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ
ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት
በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት
መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን
ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን
ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት
እንጠብቅሻለን አለብን አደራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።
ግጥም ደረጀ መላኩ መንገሻ፤ ዜማ ሰሎሞን ሉሉ ምትኩ
መያያዣዎች
ለማስተካከል- የዜግነት ክብር (ASF FILE) Archived ዲሴምበር 28, 2005 at the Wayback Machine