ወንጭፍ አዘዕርትን ከወፍ ጥቃት ለመጠበቅ የሚጠቅም መሳሪያ ነው። ይህ መሳሪያ ከገመድ የሚሰራ ሲሆን ለጠጠር የመያዣ ቦታ አለው። እንዲሁም ለመወርወር እንዲያመች ሁለት ጫፎች ሲኖሩት አንደኛው የገመዱ ጫፍ ለጣት ማስገቢያ የሚሆን ቀዳዳ ይሰራለታል።