ወልድ
እግዚአብሔር ወልድ ከሶስቱ ቅዱሳን አካላት አንዱ ሲሆን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ ስለ ሰው ልጆች ሲል ሞቶ ተገርፎ እና በመስቀል[1] ተስቅሎ ያዳናቸው ሲሆን በኋላኛዕ ዘመን በትንሳዔ ዘጉባኤ ሙታንን ከመቃብር ነፍስ ዘርቶ ኃጥአ(ፍየሎችን) በግራ ጻድቃን(በጎቹን) በቀኝ የሚያቆመው ጻድቃንን መንግስተ ሰማያት እየተባለች የምትጠራውን እየሩሳሌም ሰማያዊትን የሚያወርሰው ይህ ቅዱስ አካል ነው