ወልደያ ወይንም ወልዲያደሴ ሰሜን 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል[1]

ወልደያ
ወልደያ ከተማ
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል አማራ ክልል
ዞን ሰሜን ወሎ
ከፍታ 2,112 ሜትር
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 46,139
ወልደያ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ወልደያ

11°49′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°36′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥና ዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶች የሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡

ወልድያ

ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥና ዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶች የሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡ መገኛነቷን ስንቃኝም ከአዲስ አበባ 520 ኪ.ሜ፣ ከባህር ዳር 360 ኪ.ሜ፣ ከላልይበላ 168 ኪ.ሜ፣ ከመቀሌ 260 ኪ.ሜ፣ ከጅቡቲ ወደብ (በአፋር በኩል) 553 ኪ.ሜ እርቀት የተነሱ ሁሉ የሚገናኙባት ናት፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የራስ ወሌ ብጡል ቤተ-መንግሥት በነበረበት በመርጦ አቅጣጫ እዜት በርን አቋርጦ በመገንባት ላይ ያለው የደላንታ መንገድም ከተማዋን በማማከል 5ኛ ሀገር አቋራጭ መንገድ መሃል ከተማዋን ያቋርጣል፡፡

ታሪክ ለማስተካከል

ከተማው በታሪካዊ ቦታወች የተከበበ ሲሆን በ1834ዓ.ም. ወልደያን ጎብኝቶ የነበረው ሚስዮኑ ጆዓን ሉዊግ ክራፍ ደጅአዝማች ፋሪስ አሊጋዝ እና ወንድሙ እና ካሊድ ብሩ አሊጋዝ መምሪያቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው እንደነበር ዘግቦት ይግኛል። ሁለቱ ወንድማማቾች በዚያን ወቅት ወረ ይመኑን ለመውጋት ተንቀሳቅሰው እንደነበር ይገልጻል፡፡[2]

በ1880ዎቹ ወልደያ ለዝሆን አደን ተስማሚ ስለነበር በታሪክ ተጠቃሽነት አለው። ከ1880ዎቹ እስከ 1950ዎቹ ወልደያ የየጁ አውራጃ ማዕከል ነበር[1]። በዚህ ወቅት፣ የወልደያ ሆስፒታል በ1929 ዓ.ም በኮንተራክተሩ M.C.M. Pollera ተገነባ። ሆስፒታሉ ሰፊ ቦታ የያዘና ለሰራተኞች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ያለውም ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሆሰፒታሉ ለከተማው ነዋሪና ለተጎራባች ከተሞች (ላሊበላ፣ አላማጣ፡አፋር፣ ጎንደር) ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማዋ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታይባት ስትሆን በሶስት አቅጣጫ የሚነሱት አውራ መንገዶቹዋም በአስፓልት ኮንክሪት የተሰሩ ናቸው፡፡ የ ፪፬ ሰዓት የ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፓዎር የምታገኝ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ አንድ ዘመናዊ ስታዲዮም ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ባጃጅ ታክሲዎች በአሁኑ ጊዜ ዋነኞቹ የህዝብ ትራንስፖርት መንገዶች ናቸው፡፡

መልክዓ-ምድር እና የሥነ-ህዝብ ምጣኔ

የከተማዋ መልክዓ-ምድር አቀማመጥ ወጣ ገባና በተፈጥሮ በተራራ የተከበበች፣ ጥቁር ውሃ እና አላውሃ በዙሪያዋ የሚፈሱባት ስትሆን አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ ምጣኔም12,213.56 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6,445 በአሁኑ ማስተር ፕላን የፕላን ምድብ የተካተተ ነው፡፡ ከምድረ ወገብ በ11,050 ሰሜን ኬክሮስና ከ39,046 ምስራቅ ኬንትሮስ መካከል ስትገኝ ከባህር ጠለል በላይ 2,112 ሜትር ከፍታ አላት፡፡ የዓየር ንብረቷም 1% ደጋማ፣ 5% ቆላማ፣ 94% ወይና ደጋ ነው::

በ ከመሬት መቀማት ጋር በተነሳ የቀዳማዊ ወያኒ አመጽ ተብሎ በሚታወቀው የ1940 አመጽ ከተማው ላይ በየጁወች ጥቃት ሲደረስ፣ እስር ቤቱ ተከፍቶ እሰረኞች ተለቀቁ። ሆኖም አመጹ የተሳካ አልነበረም [3] አለም አቀፍ ሃብታም በመሆኑ የሚታወቀው መሀመድ አላሙዲ በ1950ወቹ ለ10 አመት በወልደያ እንዳደገ ይጠቀሳል። ጥቅምት 8-9፣ 1980 ከተማዋ በደርግ አውሮፕላን ብትደበደብም የሞተ ሰው ግን አልተዘገበም።[4]

ከዚህ በተረፈ ወልደያ ላይ የሚገኙት አኖማ ማርያም (በዛፎች ተሸሽጎ ዋሻ ውስጥ የተደበቀ ቤ/ክርስቲያን[5]) እና ወልደያ ገብርኤል ለአካባቢው ታዋቂነትን ይሰጣሉ። ገነተ ማርያምም ከወልደያ ብዙ ሳይርቅ ይገኛል።

የሕዝብ ስብጥር ለማስተካከል

በ 2007 በተደረገው አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ፣ የከተማዋ የህዝብ ብዛት 46,139 ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 23,000 ወንዶችና 23,139 ሴቶች ናቸው።[6]

የወልደያ ሕዝብ ቁጥር [7]
ዓ.ም.** የሕዝብ ብዛት የተማሪዎች ብዛት
1959
8,505
1976
15,700
1984
24,500
1993
30,200
1998
42,700
2007
46,139

ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ "Local History in Ethiopia") The Nordic Africa Institute website (accessed 19 November 2007)
  2. ^ Journals of the Rev. Messrs. Isenberg and Krapf, Missionaries of the Church Missionary Society, Detailing their proceedings in the kingdom of Shoa, and journeys in other parts of Abyssinia, in the years 1839, 1840, 1841 and 1842, (London, 1843), p. 443
  3. ^ Bahru Zewde (2001). A History of Modern Ethiopia (second ed.). Oxford: James Currey. ISBN 0-85255-786-8. 
  4. ^ Africa Watch Report, Ethiopia: "Mengistu has Decided to Burn Us like Wood": Bombing of Civilians and Civilian Targets by the Air Force Archived ኦክቶበር 4, 2012 at the Wayback Machine, 24 July 1990
  5. ^ David Buxton, 1944
  6. ^ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን Archived ኦገስት 16, 2010 at the Wayback Machine, population.pdf
  7. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/vw/ORTWEL.pdf